Kishore Kumar Hits

Jemberu Demeke - 1 Melk şarkı sözleri

Sanatçı: Jemberu Demeke

albüm: Jemberu Demeke


አሁን በቃ ተናግሬአለሁ የራሴን ነገር
የዛሬ ቃላቶች ይሁኑ ለተሻለ ነገ
የተሻለ ነገ እንዳመለካከታችን ነው
በአንድ መልክ እንጓዝ ብለን ካልተመራን በቀር
አንድ መልክ በአንድነት አንድ አላማ
ሲኖር ፈር ቀዳጆች ሆነን እየጠበበ ኢላማ
ግቡን እየከተትን በተለየ ግሩም ቃና
ገና ናቸው የሚሉትን እንሁንባቸው ገናና
አዎ!
አርቆ ማሰብ ከባድ ነው
በአቋራጭ ትኬት ገዝቶ ቶሎ መድረስ ቀላል ነው
አንጠረኛው አነጣጠር ካላወቀ ከባድ ነው
አነጣጠሩን የሚያውቀው ወርቁን ፈቶ ሲጓዝ ነው
ምን!
መንገዱ ታሪክ እንድንማርበት
አይደለም እሱን ይዘን እንድንኖር በባርነት
ባርነት ማለት ለኔ አዙሪት ውስጥ መቅረት ነው
የሚስተካከለውም በአንድነት ነው

እስኪ ደግሞ የታዘብኩትን ላውጋ
ስንቱ በሆዱ የያዘውን በቃላቶች ላውጣ
ሰብዓዊነት ተብሎ ነፃነት ከተፈጥሮ ሲጣላ
ማየት ይከብደኛል ለኔ ሰብዓዊነቱ እየላላ
ማለት?
ሀሳቤን ግን አላብራራም
ላልገባው ላልተበከለው ይህንን አላጋራም
ሚገባው ተረድቶት ይለፍ ሰብዓዊነቱም ይትረፍ
ከዛ መልዕክቱን ሲያካፍል እንደኔ ቅኔ ይዝረፍ
ማለት?
ይህን ሁላ ነገር የምለው ለምንድነው?
ለ ምንድን ነው ብዬ ሁሌ ምናገረው ለምንድነው?
ለ ምንድን ነው ለ ፊደል ነው ከ ሀ በኃላ የሚመጣ
ቀጣዩ ፊደል ተመካሪ ነው ትርጉሙ እንዲመጣ
መካሪ በሉኝ አማካሪ ዋናው መልዕክቴ ይድረስ
ህዝቤ አንድነትን ተላብሶ የፈለገውን ይልበስ
ፍቅር ሰላም ጤና ተዳርሶ ለጎረቤቱ ይፍሰስ
መልክ እና አመለካከት ቀርቶ ዋናው መልዕክቴ ይንገስ

ይድረስ መልዕክቱ ለዛ ብርቱ ለሚመለከተው
መልኩን አሳምሮ ቢሆን ከንቱ ግን ምኑን ጠቀመው
ተለይቶ ቢኖርም ልዩ አርጎ ግን አልፈጠረውም
ሁሉንም የፈጠረው በእራሱ በአንድ መልክ ነው
ብል
ብናገር ቃል ነው እራስህ የምታምነው
ባለንጀራህን ብጠላ ራስህን ነው ያጣጣልከው
ያንተው መልክ እንዳንተው ሰው ሆኖ በልዩ ማንነት
ይዞ ሲመጣ አሳየው በልዩነት ውስጥ አንድነት
ምን?
አንድ መልክ
ምን!
አንድ መልክ
ይዞ ሲመጣ አሳየው በልዩነት ውስጥ አንድነት
ይዞ ሲመጣ አካፍለው ስለራስህም ማንነት
ባህል ወግህን አሳየው ዜማህን ተጫወትለት
ምን?
አንድ መልክ
ምን!
አንድ መልክ
ይዞ ሲመጣ አሳየው በልዩነት ውስጥ አንድነት
ምን?
አንድ መልክ
ምን!
አንድ መልክ
ምክንያቱም በፈጣሪ ፊት ሁላችንም አንድ ነን

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar