ከተራራው ማዶ ማዶ ማዶ ወዲያ ከእናቴ ደጅ
አለች የልጅነት ልብ ያፈራት ወዳጅ
ስንዋደድ ኖረን ኖረን ኖረን ቢያለያየን ጊዜ
እንኳን ሰውን እንባ ተናነቀው ወንዜ
ከተራራው ማዶ ማዶ ማዶ ወዲያ ከእናቴ ደጅ
አለች የልጅነት ልብ ያፈራት ወዳጅ
ስንዋደድ ኖረን ኖረን ኖረን ቢያለያየን ጊዜ
እንኳን ሰውን እንባ ተናነቀው ወንዜ
አፈር እየፈጨን ብንጋግር ብንቀምሰው
የሚቆጣንም ሰው በሌለበት
ትዝ ትዝ ይለኛል
ተኳርፈን ተጨንቀን በማርያም ጣት ታርቀን
ያሰርነው ቀለበት ለፍቅራችን ታዛ
ባንገት ልብሷ ጥለን ዝናብ ተጠልለን ስንተያይ
ትዝ ትዝ ይለኛል
ተቃቅፈን የሳቅነው ምድርን ልታሞቀው በፈካችው ፀሀይ
መቼም አይጠፋም ካይኔ የእሷ እና የኔ
መቼም አይጠፋም ካይኔ የእሷ እና የኔ
እሷን የልቤን ንግስት ሳባዊት እንስት
መቼም ማሰብ አልታክት ማሰብ አልታክት
ከተራራው ማዶ ማዶ ማዶ ወዲያ ከእናቴ ደጅ
አለች የልጅነት ልብ ያፈራት ወዳጅ
ስንዋደድ ኖረን ኖረን ኖረን ቢያለያየን ጊዜ
እንኳን ሰውን እንባ ተናነቀው ወንዜ
ማወቅ አናንቆን ሃሳብ አራርቆን
መፍትሄ ላይሆን መለያየቱ
መደማመጥ እርቆን ግለኝነት ከንቱ
እንዳልተፋቀርን ለየን ከስንቱ
ወይ እኔን አልደላኝ ወይ እሷ አልተመቻት
እንጃልኝ እንጃ መላ አጥቻለሁ
ቀን እንዳለያየን ቀን እስኪመልሰን
እንዲያው ዝም ብዬ ተስፋ አደርጋለው
መቼም አይጠፋም ካይኔ የእሷ እና የኔ
መቼም አይጠፋም ካይኔ የእሷ እና የኔ
እሷን የልቤን ንግስት ሳባዊት እንስት
መቼም ማሰብ አልታክት ማሰብ አልታክት
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri