Kishore Kumar Hits

Jano Band - Rega şarkı sözleri

Sanatçı: Jano Band

albüm: Rega


አሃዱ
ከርሞ እንደ ወይን
የጣፈጠ
ካልማዝ ከ እንቁ
እጅግ ያማረ
በቅንነት
የሚዘራ
ፍቅር ቃል ነው
አሽቶ ሚያፈራ
ለኔማ የሚስማማ
በሂወት ዘመኔ
ማን አለ ካንቺ በቀር
ድሮስ ማን ነበር
በትግስት እንዲታነፅ
የኔም ያንቺም ቤት
ታገሺው ፍቅር ያምራል
ውሎ እያደር ያበራል

ረጋ ተግ በይ
ሺ ብሬ ሺ ብሬ ሺ ብሬ
ረጋ ተግ በይ
ሺ ብሬ ሺ ብሬ ሺ ብሬ
ላልጨርስ ባንዴ ተናግሬ
ቃል በቃል ታሪኬን ዘርዝሬ
ሂወት ሲጀምር ሀ ብሎ
ኣቦጊዳን አስከትሎ
ካልተራመዱ ሁሉን ችሎ
የት ይደረሳል ተቸኩሎ
ረጋ ረጋ ተግ በይ
እንደ ነስር ከደመና በላይ
በደስታም እንድንከንፍ ወደላይ
ረጋ ረጋ ተግ በይ
መብረር ካሻሽም ወደ ሰማይ
ለማጣጣም የአርካታን ሲሳይ
ረጋ ረጋ ረጋ ተግ በይ በይ በይ
ለኔማ የሚስማማ
በሂወት ዘመኔ
ማን አለ ካንቺ በቀር
ድሮስ ማን ነበር
በትግስት እንዲታነፅ
የኔም ያንቺም ቤት
ታገሺው ፍቅር ያምራል
ውሎ እያደር ያበራል

ረጋ ተግ በይ
ሺ ብሬ ሺ ብሬ ሺ ብሬ
ረጋ ተግ በይ
ከተባለማ ፍቅር ቅር
ከንኩ አይቅር ስንቁም ቢቀር ብመር ልቤ ከቀናው ቃሉ ያውቅሉ
ዳሩ ሰው ከምር ከዓንጀት ሆዱ ፈልጎ ማግኘት መቻሉ ነው ክብሩ
ከሁሉም
ከማስረዳት መደማመጥ
ከብዙ ቃል ትንሽ ስሜት
ማንበብ መልመድ
መተራርም ይቅር ማለት
መተሳሰብ መተማመን
ለእዉነት
መከባበር መፈቃቀር
መስጠት ነው ፍቅር ማለት
ካሻን ሀገር ሄደን
ካሻን መንደር
ካሻን ስፍራ
ባሻን መንገድ
ውለን የምናድርበት
ካወቅንበት
አይደል ሌላ ፍቅር ማለት
በልባችን ያለ እውነት
ረጋ ረጋ ተግ በይ
እንደ ነስር ከደመና በላይ
በደስታም እንድንከንፍ ወደላይ
ረጋ ረጋ ተግ በይ
መብረር ካሻሽም ወደ ሰማይ
ለማጣጣም የአርካታን ሲሳይ
ረጋ ረጋ ረጋ ተግ በይ በይ በይ
ረጋ ረጋ ተግ በይ
እንደ ነስር ከደመና በላይ
በደስታም እንድንከንፍ ወደላይ
ረጋ ረጋ ተግ በይ
መብረር ካሻሽም ወደ ሰማይ
ለማጣጣም የአርካታን ሲሳይ
ረጋ ረጋ ረጋ ተግ በይ በይ በይ
ረጋ ተግ በይ

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar