ልጄ ተስፋ አትቁረጥ ሲል ቃል ከ ልቡ መዞ
በአንድ እጁ ጋሻውን በአንዱ መፅሀፍ ይዞ
በልበ ሙሉነት አባቴ ነው ያለኝ ቁም ለምታምንበት
ማንነትህ ፍቅር ብሎ እንዳሳደገኝ እውነቱ ሰውነት
ብፅፍ ስለአንተ ብናገር አይበቃም ጊዜ ያንሱብኛል ቃላት (ሰአታት)
ባሳለፍከው አስተማሪ ሆነኸኛል ጓደኛዬም ወንድሜም የኔ አባት (ባንተ ብርታት)
አውርሰኽ ክብር ሰተኸኛል ሀገር መቼም የማልተዋት (እናት የማልረሳት)
ቃልህ ነበር ብርሃን ሆኖ ከጨለማው ልቤን የመለሳት (እንዳልጠፋ በእሳት)
ለካ ያኔ ድሮ ድሮ አውቆት ነበር (እያለ)
ኖረህ እየው በል ሁሉንም ያለኝ ነገር (እያለ)
ደርሼበት ሳየው ያለው እውነት ብቻ (እያለ)
አስተውል ሁሌም አለህ ምርጫ (እያለ)
ለካ ያኔ ድሮ ድሮ አውቆት ነበር (እያለ)
ኖረህ እየው በል ሁሉንም ያለኝ ነገር (እያለ)
ደርሼበት ሳየው ያለው እውነት ብቻ (እያለ)
አስተውል ሁሌም አለህ ምርጫ (እያለ)
እኮ ሌላ ቢሆን ሰው ተቀይሮ በፈተና ኑሮ (በፈተና ኑሮ)
ባያስተውል እውነት ታሪክ ዞሮ በዋሉበት ውሎ (በዋሉበት ውሎ)
ሀቅ አንተ ነህልጄ እውቀት ጥበብ ውርስ ከሀሳብ እንድትደርስ (ከሀሳብ እንድትደርስ)
ስለሚቀየር ሁሉም ሁን የእውነት መቅደስ ነገ እንዳትወቀስ (ነገ እንዳትወቀስ)
የብራናው ቃሉ እሱ ነበር ለአባቴ ሰው ማንነቱ ትርጓሜው ስራ
ማወቅ ሲቀይረው ዘመን ሲያቀላቅል ሁሉን ያበቃል ያ ከንቱ ቆጠራ
ሲል በ ግርማ ሞገስ ዝምታ ይበልጣል ለኔ ምሳሌ እየሆነኝ (ምሳሌ እየሆነኝ)
ተምሪያለው እምነት የአገር ፍቅር ትዕግስት አባቴ ሲነግረኝ
ለካ ያኔ ድሮ ድሮ አውቆት ነበር (እያለ)
ኖረህ እየው በል ሁሉንም ያለኝ ነገር (እያለ)
ደርሼበት ሳየው ያለው እውነት ብቻ (እያለ)
አስተውል ሁሌም አለህ ምርጫ (እያለ)
ለካ ያኔ ድሮ ድሮ አውቆት ነበር (እያለ)
ኖረህ እየው በል ሁሉንም ያለኝ ነገር (እያለ)
ደርሼበት ሳየው ያለው እውነት ብቻ (እያለ)
አስተውል ሁሌም አለህ ምርጫ (እያለ)
ቃሉ አይለወጥም ነው የፀና (የፀና)
በቻለው ህይወቴን ስላቀና (እሱማ)
አንተ ነህ የኔ አባት የኔ ጀግና (ለኔማ)
አንተ ነህ የኔ አባት የኔ ጀግና (ለኔማ)
ቃሉ አይለወጥም ነው የፀና (የፀና)
በቻለው ህይወቴን ስላቀና (እሱማ)
አንተ ነህ የኔ አባት የኔ ጀግና (ለኔማ)
አንተ ነህ የኔ አባት የኔ ጀግና (ለኔማ)
ለካ ያኔ ድሮ ድሮ አውቆት ነበር (እያለ)
ኖረህ እየው በል ሁሉንም ያለኝ ነገር (እያለ)
ደርሼበት ሳየው ያለው እውነት ብቻ (እያለ)
አስተውል ሁሌም አለህ ምርጫ (እያለ)
ለካ ያኔ ድሮ ድሮ አውቆት ነበር (እያለ)
ኖረህ እየው በል ሁሉንም ያለኝ ነገር (እያለ)
ደርሼበት ሳየው ያለው እውነት ብቻ (እያለ)
አስተውል ሁሌም አለህ ምርጫ (እያለ)
ለካ ያኔ ድሮ ድሮ አውቆት ነበር (እያለ)
ኖረህ እየው በል ሁሉንም ያለኝ ነገር (እያለ)
ደርሼበት ሳየው ያለው እውነት ብቻ (እያለ)
አስተውል ሁሌም አለህ ምርጫ (እያለ)
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri