Samon Zemas - Chaw şarkı sözleri
Sanatçı:
Samon Zemas
albüm: Lewt
በህልሜ እንዳየሁት ይመስለኛል
ብዙ መንገድ እያለፍን ይታየኛል
እጅ ለ እጅ ተያይዘን
ጉዞአችን እንዳይለየን
በቀስታ ስንራመድ በ ድቅድቅ ጨለማ
ሲያበራልኝ ነበር ለኔ አይንሽ እንደሻማ
በጨለማው ሳልረበሽ በዛ ጭንቅ ሰአት
የሚያስፈራኝ እውነት ልዩ ነበር አንቺን ማጣት
ቻው እንዳትይኝ (4*)
በህልሜ እንዳየሁት ይመስለኛል
በዙሪያችን ያለው ሁሉ በእሳት ይጋያል
በእሳቱ መሀል ተቃቅፈናል
እያየነው ሞትን ግን ሰላም ይሰማኛል
ፍቅር እንደዝናብ ያቀዘቅዘኛል
አይገለኝ እሳቱ አዎ ህይወት ሆነሽኛል
ልቤን የሚሰብረው ነፍሴን የሚወስዳት
የሚያስፈራኝ እውነት አዎ ነበር አንቺን ማጣት
ቻው እንዳትይኝ (4*)
የሚያስፈራኝ ልዩ አንቺን ማጣት አዎ
የሚሰብረኝ ልዩ አንቺን ማጣት አዎ
የማልችለው ልዩ አንቺን ማጣት አዎ (2*)
የሚያስፈራኝ ልዩ አንቺን ማጣት አዎ
የሚሰብረኝ ልዩ አንቺን ማጣት አዎ
የማልችለው ልዩ አንቺን ማጣት አዎ (2*)
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri