Geremew Asefa - Chir Ale şarkı sözleri
Sanatçı:
Geremew Asefa
albüm: Nitsunesh
ጭር አለ አንቺን ያጣው ደጄ
እምባ ነው ከእንግዲህ ወዳጄ
እኔማ ሳላይሽ ከርሜ
እህ እላለው በናፍቆት ታምሜ
ሊመሽ ነው አድማሱ ጠቆረ
የልቤ ትርታ ጨመረ
እእ እህ ይከፋኝ ጀመረ
ሊመሽ ነው አድማሱ ጠቆረ
የልቤ ትርታው ጨመረ
እእ እህ ይከፋኝ ጀመረ
♪
የኔ ጎጆ የኔ ታዛ ፅልመት የወረሰው
ይቺን አለም እንዴት ልግፋት ብቻዬን ያለ ሰው
ባዶ ቤቴን ዘጋግቼ ከማንባት በቀር
ምን ምርጫ አለኝ ተፈርዶብኝ ያ'ላንቺ እንድኖር
ከአይኔ እምባ ሲቀዳ እየዋለ
አለሁኝ መኖር ከተባለ
እእ እህ ቅስሜ እንክት እንዳለ
ጥንድ ሆነው ያየው እለት በአይኔ
ይበዛል ይከብዳል ሀዘኔ
እእ እህ እንዴት ልሁን እኔ
♪
ጭር አለ አንቺን ያጣው ደጄ
እምባ ነው ከእንግዲህ ወዳ
እኔማ ሳላይሽ ከርሜ
እህ እላለው በናፍቆት ታምሜ
በመውደድ አልሰራው በደል
ከረምኩኝ በሀሳብ ስዋልል
እእ እህ አለመታደል
♪
መለየትሽን አምኖ ልቤ መቀበል ተሳነው
ጓዳ እልፍኙ መኝታውም አንቺን አስታዋሽ ነው
በትዝታሽ እጽናናለሁ በቀሪው ዘመኔ
በቃ እርሜ ነው ከአንቺ ሌላ አላፈቅርም እኔ
በናፍቆት እየተፈተንኩኝ
ተጎዳሁ ለፍቅርሽ ባዘንኩኝ
እእ እህ ዛሬስ ተሸነፍኩኝ
እንኳንስ እኔ ባለቤቱ
ናፍቆትሽ የጎዳኝ በብርቱ
እእ እህ ተርቦሻል ቤቱ
መች ይሆን አይንሽን አይቼ
በሰላም የማድረው ተኝቼ
እእ እህ መብሰልሰሌን ትቼ
እእ እህ መብሰልሰሌን ትቼ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri