Kishore Kumar Hits

Tsedi - Qoy şarkı sözleri

Sanatçı: Tsedi

albüm: Sew


የእውነት እያለ ህይወቴ
አቤት ደም ግባቴ
ነፃ መንፈሴ ሳይሞላ ኪሴ ጎድሎ እንኳን
ሰላምን ሰጥቶ የሚያስተኛኝ
እንዲያ የሚያሳምረኝ
ለካ የውስጤ ወጥቶ ከፊቴ ውበት ሆኖ
ብዬ ከሰው ልኖር ሰውን ልምሰል
የውሸት ሆንኩኝ
የዓለም ህግ መስሎኝ
ከሩቅ የወደዱኝ ስሆን እንደራሴ ተመሳስያቸው
ግራ አጋባኋቸው
ኧረ ቆይ ኧረ ቆይ ቆይ ቆይ ቆይ
ኧረ ቆይ ቆይ ዓለም
ኧረ ቆይ ኧረ ቆይ ቆይ ቆይ ቆይ
ኧረ ቆይ ቆይ ዓለም
ኧረ ቆይ!
በገባኝ ዓለም በራሴ
የኔ ነው ድክመቴ
ገማች የለውም ፈተና መውደቅ ማለፌ
የክብር ካባ ያለበሱኝ
ትለያለሽ ያሉኝ
ለካ የውስጤን ብቻ ስሰማ ሁሌ ሲያዩኝ
ብዬ ከሰው ልኑር ሰውን ልምሰል
የውሸት ሆንኩኝ
የዓለም ህግ መስሎኝ
ከሩቅ የወደዱኝ ስሆን እንደራሴ
ተመሳስያቸው
ግራ አጋባኋቸው
ኧረ ቆይ ኧረ ቆይ ቆይ ቆይ ቆይ
ኧረ ቆይ ቆይ ዓለም
ኧረ ቆይ ኧረ ቆይ ቆይ ቆይ ቆይ
ኧረ ቆይ ቆይ ዓለም
(ኧረ ቆይ ኧረ ቆይ ቆይ ቆይ ቆይ)
(ኧረ ቆይ ቆይ ዓለም)
(ኧረ ቆይ ኧረ ቆይ ቆይ ቆይ ቆይ)
(ኧረ ቆይ ቆይ ዓለም)
ዝም ሲል እንደዚህ ከራስ ጋር ብዙ ይወራል
ፀጥ ሲል በራስ ጊዜ ላይ የውጪው ግርግር ለካ ይጮሃል
ለመረዳት መጣር ሰውን መስሎ አለመሆን
የማያውቁትን ቋንቋ እንደመስማት ሆነብኝ
የማይገባኝ
ልክ ሲጠልቁ ግን በራስ ያስብላል
የውሸቴን ለምን?
የመኖር ሕግ ነው ያው ራስን መሆን
ማድረግ ማሰብ ለሰው ጥሩ ጥሩ
በቃ ግን ሰውን ማክበር ይጀምራል ከራስ
ያው ማፍቀር ሰውን ይጀምራል ከራስ
ይሻላል አደል?

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar