️ አምባሰል ️
እንከን የሌለበት ከእግር እስከ እራሱ
መተኪያ የሌለው ለ ስጋ ለ ነፍሱ
አገኘሁ አንድ ልጅ አገኘሁ አንድ ሰው
አገኘሁ አንድ ሰው አንድ ሰው መተኪያ የሌሌለው
ጥንትም አንተን ነበር ከቤቴ ስወጣ
ጥንትም አንተን ነበር ከቤቴ ስወጣ
እግሬ የተጓዘው ፍለጋ የወጣው
እግሬ የተጓዘው ፍለጋ የወጣው
አንተ ያገሬ ልጅ የአምባሰል ጉብል
አንተ ያገሬ ሰው የአምባሰል ጉብል
ማልኩኝ በጎፈሬህ የኔ ጠንበለል
ማልኩኝ በጎፈሬህ ማልኩልህ የኔ ጠንበለል
እንከን የሌበትም ምን ይወጣለታል
እንከን የሌበትም ምን ይወጣለታል
ሸጋው ያገሬ ልጅ ውበት ፈሶበታል
ሸጋው ያገሬ ልጅ ሸጋው ውበት ፈሶበታል
አክሱም ላሊበላን የፈጠረን ሰው
ጥበበኛ ነው ስል በጣም ሳደንቀው
ሰውን የፈጠረ ፈጣሪን ዘንግቸ
ውበት አሳስበኝ ይሄን ለጅ አይቸ
ምንድን ነው መለኪያው የሰው ልጅ ውበት
የሰሙትን ሰምተው አይተው ካልወደዱት
እንደ እቃ ተሰፍሮ ሰው ይለካል ወይ
የዚህ ልጅ ሰውነት ከሚዛን በላይ
ጥንትም አንተን ነበር ከቤቴ ስወጣ
ጥንትም አንተን ነበር ከቤቴ ስወጣ
እግሬ የተጓዘው ፍለጋ የወጣው
እግሬ የተጓዘው ፍለጋ የወጣው
ሽጋው ያገሬ ሰው ሰውነት የኔ አለም
ሰው ባንተ ይለካ ሰው ካንተ በለይ የለም
ከበሮውን ምቱት በገናም ይደርደር
ምንም አይለየኝም ካገሬ ልጅ ፍቅር
አንተ ያገሬ ልጅ እኔ እወድሃለሁ
በልቤ ገብተሀል እኔ እምልልሀለው
ልቤ ፈሶልሀል እንደ ወንዝ ጅረት
...ጠጣ ከፍቅሬ ወተት
ሸጋው ያገሬ ሰው ሰውነት የኔ አለም
ሰው ባንተይለካል ካንተ በላይ የለም
ሸጋው ያገሬ ሰው ሚዛኑ ሚዛኑ
እስቲ ሰወች ሁሉ ባንተ ይመዘኑ
ከበሮውን ምቱት በገናም ይደርደር
ምንም አይለየኝም ከዚህ ሰው ፍቅር
ደማምየ (11) ና ሸግየ ደማምየ(3) ና ሸግየ
ሸጋው ያገሬ ሰው ሚዛኑ ሚዛኑ
እስቲ ሰወች ሁሉ ባንተ ይመዘኑ
ልቤ ፈሶልሀል እንደ ወንዝ ጅረት
...ጠጣ ከፍቅሬ ወተት
ከበሮውን ምቱት በገናም ይደርደር
ምንም አይለየኝም ካገሬ ልጅ ፍቅር
አንተ ያገሬ ሰው እኔ እወድሃለሁ
በልቤ ገብተሀል እኔ እምልልሀለው
ደማምየ (11) ና ሸግየ ደማምየ(3) ና ሸግየ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri