Kishore Kumar Hits

Hanna Tekle - Yeazagn Yaleh şarkı sözleri

Sanatçı: Hanna Tekle

albüm: Yezelalem Fetari, Vol.2


ማን ያመልጣል ከእግዚአብሔር
ምን ይሸሸጋል ከጌታ
ቢገለጥ ታሪካችን ጉድ ነው የኛ ገመና
ባደባባይ ጨዋ ያረገን
በግል መክሮ ያሳፈረን
ዳኝነቱ ያልተገባን እኔን ጨምሮ ቤቱ ይቁጠረን
ነግ በኔ ማለት ጥሩ በተያዙበት መያዝ ሳይያዙ
ጌታ እንደሁ እሱ ይምራል ይህንንም ይቅር ይላል
ነግ በኔ ማለት ጥሩ በተያዙበት መያዝ ሳይያዙ
ጌታ እንደሁ እሱ ይምራል ይህንንም ይቅር ይላል
ምህረት የናቀ ዛሬም ይፈርዳል
በተማረው ልክ ማን ሰው ይምራል
ምህረት የናቀ ዛሬም ይፈርዳል
በተማረው ልክ ማን ሰው ይምራል
እንከን የለሽ ኑሮ የለኝም ታሪኬ ቢመረመር
ሌላው ላይ ስፈርድ ቆሜ ወድቆ እስኪሰበር
የሱን ገሀድ የኔን በቤቴ
ፍርድ ገምድሎ ይህ ማንነቴ
ብዙ የተማረ ብዙ ይምራል
ነበር ትምህርቱ ማን ግድ ይለዋል
አምላክ አርጎለት ሐጢያቱን ታሪክ
ሰው አልምር ብሎት ሆነ የእድሜ ልክ
አትፍረጅ አትፍረጅ ተይ ነፍሴ ይፈረድብሻል
አንቺ ተይ ምላሴ
እያየሽ እየኖርሽ እሱነት
እንዴት ግድ አይልሽም የሰው ሕይወት
(Melody)
የማያልፍ አውቆ የራሱን ጉድለት
አያቆም መፍረድ በሰው ማንነት
ለከፋ ቁስል እንጨት ይሰድዳል
ለታመመ ሰው ይህ መች ይረዳል
ኧረ ያዛኝ ያለ ይላል ጩኸቱ
አላሳልፍ ቢለው የሰው አንደበቱ
በሰው አፍ ተመቶ እያነከሰ
ስንቱ ተሰብሮ ከማይሆን ዋለ
ሃ-ሃ-ሃ-ሃ
(Melody)
ማን ያመልጣል ከእግዚአብሔር
ምን ይሸሸጋል ከጌታ
ቢገለጥ ታሪካችን ጉድ ነው የኛ ገመና
ባደባባይ ጨዋ ያረገን
በግል መክሮ ያሳፈረን
ዳኝነቱ ያልተገባን እኔን ጨምሮ ቤቱ ይቁጠረን
ነግ በኔ ማለት ጥሩ በተያዙበት መያዝ ሳይያዙ
ጌታ እንደሁ እሱ ይምራል ይህንንም ይቅር ይላል
ነግ በኔ ማለት ጥሩ በተያዙበት መያዝ ሳይያዙ
ጌታ እንደሁ እሱ ይምራል ይህንንም ይቅር ይላል
ምህረት የናቀ ዛሬም ይፈርዳል
በተማረው ልክ ማን ሰው ይምራል
ምህረት የናቀ ዛሬም ይፈርዳል
በተማረው ልክ ማን ሰው ይምራል

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar