ምልክት አለብኝ አንተ እንደረዳኸኝ
ተጥሎ የኖረ ያ ቁስለኛ እኔ ነኝ
ምልክት አለብኝ በሰውነቴ ላይ
ሁሉን የረሳሁት ጌታ ባንተ አይደል ወይ
ምልክት አለብኝ አንተ እንደረዳኸኝ
ተጥሎ የኖረ ያ ቁስለኛ እኔ ነኝ
ምልክት አለብኝ በሰውነቴ ላይ
ሁሉን የረሳሁት ጌታ ባንተ አይደል ወይ
ባንተ ነው ጌታ ባንተ ነው
ቁስለኛው ተነስቶ ሰው የሆነው
ባንተ እኮ ነው ጌታ ባንተ ነው
ምስኪኑ ተነስቶ ሰው የሆነው
ጎዳና ላይ ጎዳና ላይ
እንዳላየ ሆኖ ስንቱ አልፎኝ የለ ወይ
ለየት ይላል ዛሬስ የገጠመኝ
ሰው ቢርቅ እኔ አለሁ አለኝ
ጎዳና ላይ ጎዳና ላይ
እንዳላየ ሆኖ ስንቱ አልፎኝ የለ ወይ
ለየት ይላል ዛሬስ የገጠመኝ
ሰው ቢርቅ እኔ አለሁ አለኝ
ይህማ ይወራ ይህማ ይነገር
አንተ ባትደርስልኝ ምን ይውጠኝ ነበር
ምን ይውጠኝ ነበር
ይህማ ይወራ ይህማ ይነገር
ጌታ ባትደርስልኝ ምን ይውጠኝ ነበር
ምን ይውጠኝ ነበር
ኧረ እንዴት እሆን ነበር
የረዳኝ ጌታዬ ይክበር
እስኪ እንዴት እሆን ነበር
ያገዘኝ ጌታዬ ይክበር
እኮ እንዴት እሆን ነበር
የረዳኝ ጌታዬ ይክበር
ያቀረቀረ ተስፋው ተሟጦ
በቤተ መቅደስ ደጅ ተቀምጦ
ከሚገባና ከሚወጣው ሰው
እየለመነ ፊት የገረፈው
እኔው ነኝ ያ ሰው
ድንገት ተነስቶ ከመቅደስ ገባ
የሚያየው ሁሉ ግራ እስኪጋባ
አመሰገነ በአደባባይ
ምን ነካው የሚል ማነውስ ከልካይ
ማነውስ ከልካይ
ተመስገን ይላል ከፍ በል ይላል
እሱም እንደ ሰው ወግ ማዕረግ አይቷል
ተመስገን ይላል ከፍ በል ይላል
እሱም እንደ ሰው ወግ ማዕረግ አይቷል
ተመስገን ይላል ከፍ በል ይላል
እሱም እንደ ሰው ወግ ማዕረግ አይቷል
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri