የመዉደድ ጭንቀቱን ሲያዉቀዉ ልቦናሽ
የመዉደድ ጭንቀቱን ሲያዉቀዉ ልቦናሽ
ብቅ በይ የሀገር ልጅ ነይ ደኑን ጥሰሽ
አንቺ የሀገሬ ልጅ የወንዜ መለስ
እንዴት እችላለዉ አይን እምባ ሲያፈስ
ከሰዎች ልዩነት አለዉ አቋምሽ
ከሰዎች ልዩነት አለዉ አቋምሽ
አልረሳም አለኝ ፈፅሞ ገፅሽ
የመዉደድ ጭንቀቱን ሲያዉቀዉ ልቦናሽ
የመዉደድ ጭንቀቱን ሲያዉቀዉ ልቦናሽ
ብቅ በይ የሀገር ልጅ ነይ ደኑን ጥሰሽ
አልናገር በአዋጅ መላዉ ጨነቀኝ
አዉሬ ሊያስበላኝ ነዉ ፍቅር እጄን ይዞኝ
የቀኑማ ቀን ነዉ ሰዉ ያስታምመኛል
የቀኑማ ቀን ነዉ ሰዉ ያስታምመኛል
የለሊቱን ነገር መቻል አቅቶኛል
የመዉደድ ጭንቀቱን ሲያዉቀዉ ልቦናሽ
የመዉደድ ጭንቀቱን ሲያዉቀዉ ልቦናሽ
ብቅ በይ የሀገር ልጅ ነይ ደኑን ጥሰሽ
መንገዱ ጠፍቶሽ ነዉ ወይስ እረሳሺኝ
የፍቅርሽ ምርኮኛ እኔን አድርገሽኝ
በፍቅር ይሉኝታ ፈፅሞ አይግባሽ
በፍቅር ይሉኝታ ፈፅሞ አይግባሽ
ብቅ በይ የሀገር ልጅ አይ ደኑን ጥሰሽ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri