እባክሽ እባክሽ ታረቂኝ ተይ አታስጨንቂኝ (×2)
ለፍቅር መለኪያ ቢኖረው ደረጃ
አንቺን የምትበልጥ መገኘቷን እንጃ
እርቀሽ እርቄሽ ከምትናፍቂኝ
በቅርብ እንዳገኝሽ እባክሽ ታረቂኝ
እባክሽ እባክሽ ታረቂኝ ተይ አታስጨንቂኝ(×2)
አምናለሁ ማኩረፍሽ የምር እንዳይደለ
ይቅር ተባብለን ብንኖር ምናለ
ምናልባት ይሆናል ሳላውቅ አስቀይሜሽ
የጥንቱን አስታውሽው ጨካኝ አይሁን ልብሽ
እባክሽ እባክሽ ታረቂኝ ተይ አታስጨንቂኝ(×2)
ቀንም እንዳልሰራ ለሊቱን በሀሳብ
ባንቺ ፍቅር ብዛት እኔ ለምን ልራብ
ስለዚህ አስቢ እስኪ በጥሞና
ይታደስ ፍቅራችን ይጠቅመናልና
እባክሽ እባክሽ ታረቂኝ ተይ አታስጨንቂኝ(×2)
ካንቺ መለየቱ ሆነብኝ ዱብዳ
እዘኝልኝና ድረሽ ሳልጎዳ
ጠላት እንዲከፋው ደስ እንዲለው ወዳጅ
አንቺ እኔን ታረቂኝ ይቅርብን አማላጅ
እባክሽ እባክሽ ታረቂኝ ተይ አታስጨንቂኝ(×2)
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri