ምን ልሁን ባላገሩ
ምን ልሁን ወደ ሀገሩ
እሆሆሆሆሆ
ያንገበግበኛል አቤት እንደ ልጅነቴ አዬ
አዬ አዬን አዬዬዬ
አንቺን ከፍቶሽ ከማይ አቤት ይሻለኛል ሞቴ አዬ
አዬ አዬን አዬዬዬ
ምን ልሁን ንገሪኝ አቤት አንቺ ሀገሬ እናቴ አዬ
ምን ልሁን
ምን ልሁን ሆይይይ
ምን ልሁን ሆይ ሆይ
ምን ልሁን ሆይይይ
ምን ልሁን ሆይ ሆይ
ሆሆሆ ሆዴ ሆዴ ሆዴ
አትረበሽብኝ አትከፋ ሆዴ
የፈጠራት ጌታ ዝም ይላታል እንዴ
ድሮስ ጠባቂዋ እርሱ አይደለም እንዴ
ኧረ እናቴ ሆዴ ኧረ ሀገሬ ሆዴ
ልበል ደፋ ቀና ምን ላርግልሽ ጉዴ
ለመቼ ሊሆን ነው ካአንቺ መወለዴ
በእናት እና በሀገር ይቀለዳል እንዴ
ብትኖሪ አይደለም ወይ መክበር መወደዴ ተይማ
የቀለምሽ ህብረት መዋቢያ
የታሪክሽ ስምረት መክበሪያ
የዓለም ፍጥረት ቅሪት ማደሪያ
ቀኑብሽ ቅድስት ኢትዮጵያ
የሃይማኖት ፍቅር መማሪያ
የጥበብ መነሻ ማደሪያ
የፍቅራችን ኪዳን ማሰሪያ
ኑሪልን እናት ኢትዮጵያ
የቃልኪዳን ቤትሽ የወይራው ምሰሶ
የከፍታሽ ጣሪያ ያልታያቸው አንሰው
ይሰቃያሉ እንጂ መች ሊያወርዱሽ ደርሰው
ከላይ መሆንሽን ያልተረዱሽ ከሰው
እንኳን ያለሽ ሊጎል ሊጠብ ማደሪያሽ
ገና አለም ይሆናል የመክበሪያው ስፍራሽ
ዘርሽን ባርኮ ነው አምላክሽ የሰራሽ
ኢትዮጵያችን ገና ትሰርጋለች ጭራሽ
ምን ልሁን ምን ልሁን
ሆሆሆ ሆዴ ሆዴ ሆዴ
አትረበሽብኝ አትከፋ ሆዴ
የፈጠራት ጌታ ዝም ይላታል እንዴ
ድሮስ ጠባቂዋ እርሱ አይደለም እንዴ
ኧረ እናቴ ሆዴ ኧረ ሀገሬ ሆዴ
ልበል ደፋ ቀና ምን ላርግልሽ ጉዴ
ለመቼ ሊሆን ነው ካአንቺ መወለዴ
በእናት እና በሀገር ይቀለዳል እንዴ
ብትኖሪ አይደለም ወይ መክበር መወደዴ
ምን ችግር ቢገጥመው ባላገር
ተስፋ አይቆርጥም ከቶ ስለ ሀገር
ይማከር ሰክኖ ይነጋገር
ይጥፋልን ችግር ብሎ ነገር
እሸት ወተት ይትረፍ ቤታችን
ይደጉ ይፍኩ ልጆቻችን
አንድ ይሁን ይፋቀር ልባችን
ካፈሩ ሰው ነው ገንዘባችን
ጠፍተን ከርመን እንኳን
እርም ሆኑ ሲለን ሰው
አውደ ዓመቱ ሲደርስ
ደጅሽ የምንደርሰው
የእናት መስተፋቅር
መች ለቆን መንፈሱስ
ልጆችሽ መጥተናል
ተይዘን ባንቺ ሱስ
ይመስክር ባላገር አፈርሽን ሚቀምሰው
ጣዕምሽን ቢያውቀው ነው ስላንቺ የሚያለቅሰው
ተቃቃሩ ብለህ ደስ እንዳይልህ ጠላት
ያውል አመል ነው እንጂ
ማን ቀልድ ያውቃል በእናት
ቴዎድሮስ ቢጋደል ዮኃንስ ቢቀላ
ምን ጉዳይ አላቸው ከሀገሬ ሌላ
እምዬ ምኒሊክ ደጅ አዝማች ገረሱ
ባንቺ ቀልድ አያቁም ምን ሊነካሽ እሱ
ያ በላይ ዘለቀ ባልቻ አብዲሳ አጋ
ጀግኖችሽ እያሉ ማን ሊደርስ አንቺ ጋር
እነ ዑመር ሰመተር ፉራካ ኦጦና
ስንቶቹን ላንሳልሽ አንቺ ወላድ ጀግና
ባይ ወጉን አይደለም በነጭ ያልተገዛን
ተቸግረው እንጂ ስንሞት እየበዛን
ስንት ሺህ ጀግኖችሽ ከነፈረሳቸው
ለፍቅር ሞተዋል ላንቺ ለእናታቸው
ምን ልሁን ባላገሩ
ምን ልሁን ወደ ሀገሩ
ምን ልሁን ባላገሩ
ምን ልሁን ወደ ሀገሩ
ምን ልሁን ባላገሩ
ምን ልሁን ወደ ሀገሩ
ምን ልሁን ባላገሩ
ምን ልሁን ወደ ሀገሩ
ምን ልሁን ባላገሩ
ምን ልሁን ወደ ሀገሩ
ምን ልሁን ባላገሩ
ምን ልሁን ወደ ሀገሩ
ምን ልሁን ባላገሩ
ምን ልሁን ወደ ሀገሩ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri