አንቺ ሰው
ልገልፅሽ ቃላት አጣሁልሽ
ጠፋና የምለዉ
ገና ሳልጀምረው
ልንገርሽ እማ
እንድታውቂው ልሞክር
ቃል ልደረድር
ከየት ብዬ ልጀምር
እ.ም. ልጀምር ሄይ ሄይ
ልንገርሽ እማ
ልገጥምልሽ ሞከርኩና
ቤቱን ከየት ልምታው
ያንቺ ፍቅር ቤት አይበቃው
እ.ም. አይበቃው ሄይ ሄይ
ልንገርሽ እማ
እችል መስሎኝ እዘርፈው
ቃላት ገጣጥሜ
እኔን ብሎ ባለ ቅኔ
ድንቄም ባለ ቅኔ ሄይ ሄይ
ልንገርሽ እማ
አቅቶኛል ልገልፅሽ
እንኳን ልክስሽ
ብቻ ይወድሻል ልጅሽ
አይ ልጅሽ
አይ ልጅሽ ይወድሻል
ልጅሽ እምዬ
ሞትን ባስቀረው ላንቺ ብዬ
እማማ... ዬ እማማ... ዬ
ቃላቶች ስላጣሁልሽ
ሙዚቃዬ ፍቅሬን ይንገርሽ
እማማ... ዬ እማማ... ዬ
እማዬ
አዬ
በላይ በላይ ላንቺ
ደስታውን ድርብርብ ያርገው
የሰማዩ ልቡ የታመነው አሜን
በላይ በላይ ላንቺ
ደስታውን ድርብርብ ያርገው
የሰማዩ ልቡ የታመነው አሜን
ልንገርሽ እማ
ዛሬ ትልቅ ሰው ተብዬ
ለሰው ልታይ እንጅ
ላንቺ የማላድግ ልጅ
ሁሌም ህፃን ልጅ
ሄይ ሄይ
ልንገርሽ እማ
ያጠባሽው ቢሰላማ
ማን ሰው ይችለዋል
ባንቺ ሲሉት ብቻ ይተዋል
ስምሽ ያበርደዋል ሄይ ሄይ
ልንገርሽ እማ
ድጋሚ ልፍጠር ብሎ
ምርጫ ቢያቀርብልኝ
አንቺን እለው ድገምልኝ
አይ ድገምልኝ ሄይ ሄይ
ልንገርሽ እማ
አድጌያለው በእጆችሽ
ሰው ነኝ በምክርሽ
ጠብቆኛል ፀሎትሽ
ልቤ አንቺ ነሽ
እወቂው ይወድሻል ልጅሽ እምዬ
ሞትን ባስቀረው ላንቺ ብዬ
እማማ... ዬ እማማ... ዬ
ቃላቶች ስላጣሁልሽ
ሙዚቃዬ ፍቅሬን ይንገርሽ
እማማ... ዬ እማማ... ዬ
አደዬ
በላዬ
እናናዬ
ልንገርሽ...
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri