ጥያቄ
ከአለም በፊት ከሀገር እና ሠው
በፈጠረን ፊት ሚበልጥ ማነው
ጥያቄ
በፈጠረን ፊት ከበለጠ ሠው
እንደአምላክ ባስብ ስህተቱ የት ነው?
ጥያቄ
የቱን ባስቀድም ሠው ወይስ ሀገር
የሀገሬ ነገር ይሞላ ነበር
ጥያቄ
ሀገሬን ሀገር ካደረገማ
ሠውን ላስቀድም ሠው ልሁንና
እንደአድዋ እንደዚያ ሰሞን
ሀገሬ አማረች ሠው ለሠው ሲሆን
ለካ አድዋ ለሠው ልጅ ነበር
ለነፃነቱ የሆነው ሀገር
አሉ ሚኒልኩ
መልዕክቱን ሲልኩ
አሉ ሚኒልኩ
መልዕክቱን ሲልኩ
ሚኒልኩ
ሚስትህን ሚቀማህ
ማህተብ የሚያወልቅ
ልጅህን ሊወርሰው
ማንነት ሊያርቅ
ባሪያው ሊያረግህ
ቆሟል ከደጅህ
ሀገርህ ሚስትህ ናት
ደግሞም እናትህ
ሀገርህ ልጅህ ናት
ደግሞም ማህተብህ
ሠው ሆይ ተከተለኝ
ሠው አርገኝ ላርግህ
ሠው አርገኝ ላርግህ
እናስ ይህ ምን ይላል
ሀገር ሲተነተን የሠው ልጅ ይሆናል
ይሆናል
ይሆናል
አድዋን ለሀገር ያደረገው ማነው?
አድዋ ለሠው ልጅ
አድዋ ለኔ ነው
ለኔ ነው
ሚስትም ትሁን እናት
ልጅም ማለት ሁሉም ሠው
የሂጃብም የማህተብም ተስፋው ማሰሪያው ሠው ነው
ድንግሏም እርሱም የሠው ልጅ
ሠው ጠልተው ማህተቡ ላይበጅ
ሠው ላፍቅር ጀግና ልሁንና
ልቤ ላይ ነው የዛሬ አድዋ
ሠከላ አባይን ወለደች
እናቴም እኔን
አድዋ ከራስ ጀመረ
እራሱን ያሸነፈ
ለሠው ተረፈ
ሁሉም ትውልድ አድዋ አለው
የኔም አድዋ ልቤ ላይ ነው
ጀግና ማለት
ይቅር ባይ ነው
ቂም በሆዱ ከሰበቀ
ጎጃም ሠው ካላረቀ
ከይቅርታ
ከራቀ
በላይ መቼ ዘለቀ
ይቅር ካላወቅንማ
ዮሀንስ ለሀገር ወድቆ ሲሰዋ
ቴዎድሮስ መቅደላ የጠጣት ፅዋ
ለከንቱ ነዋ
ባልቻ ዛሬም ይነፍሳል
አሉላ ዛሬም ይደርሳል
ቃል እየተማዘዝነ
እኛው በኛው አንሰን ከተራከስነ
በእነሱ አድዋ ድል አርገናል
ግን የኛን አድዋ ተሸንፈናል
ተው
አድዋን ለሀገር ያደረገው ማነው
አድዋ ለሠው ልጅ አድዋ ለኔ ነው
ሁሉም ትውልድ አድዋ አለው
የኔም አድዋ ልቤ ላይ ነው
ጀግና ማለት
ዛሬ ዛሬ
ይቅር ባይ ነው
ሠከላ አባይን ወለደች
እናቴም እኔን
ሠከላ አባይን ወለደች
እናቴም እኔን
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri