Kishore Kumar Hits

Rophnan - Senaye şarkı sözleri

Sanatçı: Rophnan

albüm: Sidist (VI)


ይሰማል ከሩቅ ሆታ እና እልልታ
ይነዳል እሳት ይሳባል ቃታ
መጥተሻል መሰል ገብተሻል ከቤት
ልገስግስ ከዚህ ይቀራል እንዴት
ይላል እርግፍ እርግፍ
እስክስታው ሲደለቅ ሰምቶ ልቤም ጥድፍ ጥድፍ
ናፍቆት ያበረረኝ መናኝ ደርሼ አንቺን ላቅፍ
ናፍቆት ያሰከረኝ ወዳጅ ስሜን ባንቺ ላጽፍ
ላጽፍ
ላይሽ ዳግም ልቤ ይመታል ባንቺ ስም ዛሬም
ያንቺን ባላውቅም ሳይታከም ውስጤ ባይኖችሽ
ሳላይሽ አላድርም
ክፈች በሩን ልግባ ከቤትሽ ሳልጠራሽ ዳግም
ዳግምዬ ዳግም
ሰናዬ
ያምራል ሌቱ ደምቆ ሰማዬ
ደስታ ፍቅር ቤቱን የሞላው
ሰናይ ብለው ሲጠሩሽ ሰማው
እ አይ ሰማው አይ ሰማው
ሰነዋይ
ለብሰን መተናል አንቺን ልናይ
እፍን እፍን ይወዳል ቤትሽ
ሎሚውን ጣልኩት ከደረትሽ
አ ደረትሽ
ደረትሽ
መጥተን ከቤት ገብተን
ለአምዬም ጎንበስ ላብዬም እጅ ነስተን
ጭፈራው ደራ ገባች መሃላችን
ጸሀይ ለሌቱ ደምቀሽ አበራሽን
ያዘው ገባ ጎበዝ
ይላል ከዚም እስከዚያ ድረስ
አልተዋጋም አድርሶ ፈረስ
ማነው የረታ የቀናው በለስ
ያሸነፈ
ያሳመነ ሰው አይኗን የጠለፈ
የማረከ ማነው ቀልብ ያከነፈ
የታመነ ማነው ልብ ያተረፈ
እኔው
ሮፍናን ስሜው
ከቃሉ ውጪ ምኔው
ይዘርፋል ይወርዳል ቅኔው
ፍቅር ጥሜው
ፍሬው
ነበር ጥሬው
ከቶ አይበርድ ይሞቃል ሰኔው
ደስታ ነው ከቆየሽ ከኔው
አሸነፈች ሲሏት አሸነፋት
አይኔ ካንቺ በቀር ልቤ ካንቺ ጋር ናት
ፈንዲሻ ፈንዲሻ ከላይ በትኑላት
ለምሽቷ ንግስት እስኪ እልል በሉላት
እልል በሉላት እስቲ እልል በሉላት
እስቲ እልል በሉላት
እስቲ እልል በሉላት
ሰናዬ
ያምራል ሌቱ ደምቆ ሰማዬ
ደስታ ፍቅር ቤቱን የሞላው
ሰናይ ብለው ሲጠሩሽ ሰማው
እ አይ ሰማው አይ ሰማው
ሰነዋይ
ለብሰን መተናል አንቺን ልናይ
እፍን እፍን ይወዳል ቤትሽ
ሎሚውን ጣልኩት ከደረትሽ
አ ደረትሽ
ደረትሽ
አሸነፈች በለው
አሸነፋት በለው በለው
አሸነፈች በለው
አሸነፋት በለው በለው
ሲሉን
አሸነፈች በለው
አሸነፋት በለው በለው
አሸነፈች በለው
ሲሉን
አሸነፋት
ገባሁ
እስክስታው ይደቃል ተውባለች ይላል
ችቦ አይሞላም ወገቧ
ከልብሽ ለመግባት ያጎብዳጁ መአት
ማር እሸት ነው ቀለቧ
እኔማ ቀለብሽ ማርእሸት ነው ብዬ መቼ ተሞኘሁኛ
የማይቀመሰው የወንዶቹ ቁና ሆኜ ተገኘሁኛ
አንድ ነው
ቃታውን ሳብ ነው
አንድማ ያጣላል ለፍቅር ሁለት ነው
አንድ ነው
ቃታውን ሳብ ነው
መሰሰት የለም ላንቺማ ሰናዬ ተረክ ነው
አባቷ ሚሏት አይናለሜ
እናቷ ሚሏት ሰርካለሜ
ወንድም እህቶቿ እህትአለሜ
እኔ አቀረብኳት ብዬ ሀገሬ
እንደ ሹሩባዋ ጥብቅ አልባሶዋ
ባንገቷ ወረድኩኝ ወርቅህዛባዋ
እያልኩኝ ስሟን
ሰናዬ
ያምራል ሌቱ ደምቆ ሰማዬ
ደስታ ፍቅር ቤቱን የሞላው
ሰናይ ብለው ሲጠሩሽ ሰማው
እ አይ ሰማው አይ ሰማው
ሰነዋይ
ለብሰን መተናል አንቺን ልናይ
እፍን እፍን ይወዳል ቤትሽ
ሎሚውን ጣልኩት ከደረትሽ
ሮፍናን
Drop it again boi

ሰናዬ ሰናዬ
የ ሰናይ
ነደዋይ ተመሰል

Nonstop Hip Hop
Roph-nan
Rophnan

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar