Kishore Kumar Hits

Nhatty Man - Sherngai şarkı sözleri

Sanatçı: Nhatty Man

albüm: Man


ሸንጋይ ሸንጋይ ምላሴ
አኑረኝ ልደር ለነብሴ
እዉነቱን ዉስጤ እያወቀዉ
አንደበቴ ሸፍኖ ሸኘዉ
ሸንጋይ ሸንጋይ ምላሴ
አኑረኝ ልቆይ ለነብሴ
እዉነቱን ዉስጤ እያወቀዉ
አንደበቴ ሸፍኖ ሸኘዉ
ላይረባዉ ላይበጀዉ ላይረዳዉ ይሄ ሁሉ
ስም ላይጨምርለት ታዉቃለህ መባሉ
የጠቀምኩት መስሎኝ ያተረፍኩ ለራሴ
ለክፉ ሸኘሁት በገዛ ምላሴ
የሚያዉቀዉ እዳዬን ሳይዋሽ ሂሊናዬ
ምን ይሉኝን ሸሽቶ ደለለዉ ስጋዬ
እዉነቱን የሚያዉቀዉ ሳይዋሽ ሂሊናዬ
ምን ይሉኝን ፈርቶ ደለለዉ ስጋዬ
ሸንጋይ ሸንጋይ ምላሴ
አኑረኝ ልደር ለነብሴ
እዉነቱን ዉስጤ እያወቀዉ
አንደበቴ ሸፍኖ ሸኘዉ
ሸንጋይ ሸንጋይ ምላሴ
አኑረኝ ልቆይ ለነብሴ
እዉነቱን ዉስጤ እያወቀዉ
አንደበቴ ሸፍኖ ሸኘዉ
ላይረባዉ ላይበጀዉ ሀቁን መሸሸጌ
ከህልሙ ላያዘልቀዉ የዛሬን መሳቄ
ቀን ሲሄድ ቀን ሲነጉድ ጸጸት አይሁን ትርፌ
ይብቃ በል አንተም ተዉ ታረም አንደበቴ
የሚያዉቀዉ እዳዬን ሳይዋሽ ሂሊናዬ
ምን ይሉኝን ሸሽቶ ደለለዉ ስጋዬ
እዉነቱን የሚያዉቀዉ ሳይዋሽ ሂሊናዬ
ምን ይሉኝን ፈርቶ ደለለዉ ስጋዬ
ሸንጋይ ሸንጋይ ምላሴ
አኑረኝ ልቆይ ለነብሴ
እዉነቱን ፈርቶ ሳይነግራ
አንደበቴ እሷንም ሸኛት
ሸንጋይ ሸንጋይ
ሸንጋይ ሸንጋይ
ሸንጋይ ሸንጋይ
ሸንጋይ ሸንጋይ
ሸንጋይ ሸንጋይ

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar