የሆነበትን ሲያወጋው ልቤ
ሳወጣ ሳወርድ በሀሳቤ
አመት አይመስልም ካንተ ጋራ
ከራሴ ሳወራ
እድሜልክ ያህል ረዘመብኝ
አንድ አመታችን ሺ ሆነብኝ
ግለ ታሪኬን ያሰፈርኩበት
ይህን ጉድ ይዟል ይህ ወረቀት
፷ እንቅልፍ አልባ ቀናት
፸ ከባድ የራስ ምታት
ባንተ ምክንያት ነው ባንተ አመት
ካይኔ ሀይቅ ያህል እንባ
አንዲት የፍቅር አበባ
የሆነው ሁሉ አንዱ አይረባ
ታዲያ ቆሜ ሳስበው (ሳስበው)
ጉድ ነው ይሄስ ላንድ ሰው (ላንድ ሰው)
አመት ዝንትአለም ነው እንዴ (ነው እንዴ)
ከሀገር ምን ቢሰፋም ሆዴ
፫፻፷፭ ቀናት
ንትርክ ጭቅጭቅ ነው ቅናት
የኖርኩበት ጭንቀት ስንት አይነት
ካፍህ ፫፻ ይቅርታ
አንድም የረባ ትዝታ
ካመት ፪ ቀን ሳቅ ጨዋታ (ሳቅ ጨዋታ)
♪
የሆነበትን ሲያወጋው ልቤ
ሳወጣ ሳወርድ በሀሳቤ
አመት አይመስልም ካንተ ጋራ
ከራሴ ሳወራ
ወዳጅ ነን እንጂ ጠላት ነን እንዴ
የምንግባባው ከስንት አንዴ
እንዴት ዘለቅን ኧረ እስከዛሬ
አብረን ነን ያልነው ከንቱ ወሬ
፷ እንቅልፍ አልባ ቀናት
፸ ከባድ የራስ ምታት
ባንተ ምክንያት ነው ባንተ አመት
ካይኔ ሀይቅ ያህል እንባ
አንዲት የፍቅር አበባ
የሆነው ሁሉ አንዱ አይረባ
ታዲያ ቆሜ ሳስበው (ሳስበው)
ጉድ ነው ይሄስ ላንድ ሰው (ላንድ ሰው)
አመት ዝንትአለም ነው እንዴ (ነው እንዴ)
ከሀገር ምን ቢሰፋም ሆዴ
የኔ የኑሮ ማስታወሻ
ባየው እስከመጨረሻ
ሙሉ የራስ ምታት ማስታገሻ
ፍቅር ያልነውም ለስሙ
የኛስ ጭጋግ ነው ቀለሙ
ከዚህስ ብቸኝነት በስንት ጣሙ
ታዲያ ቆሜ ሳስበው (ሳስበው)
ጉድ ነው ይሄስ ላንድ ሰው (ላንድ ሰው)
አመት ዝንትአለም ነው እንዴ (ነው እንዴ)
ከሀገር ምን ቢሰፋም ሆዴ
ታዲያ ቆሜ ሳስበው (ሳስበው)
ጉድ ነው ይሄስ ላንድ ሰው
አመት ዝንትአለም ነው እንዴ
ከሀገር ምን ቢሰፋም ሆዴ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri