በስራዋ ክፋት ሞት ሲፈረድባት
አለም ጠፍታ ነበር ፍል ውሀ ዘንቦባት
በምህረት ቃልኪዳን በቀስተዳመና
ስለ ኖህ ተረፈች አለም እንደገና (አለም እንደገና)
ይቅር በለን (ይቅር ይቅር በለን)
ይቅር ይቅር በለን (ይቅር ይቅር በለን)
ይቅር በለን (ይቅር ይቅር በለን)
ዛሬም አለን በኖህ ዘመን (ዳግም በሎጥ ዘመን)
ተጸጸጥኩ እያለ (እያለ) ሰውን በመፍጠሬ
የነገረንን ቃል የት አረግነዉ ዛሬ (ዛሬ ዛሬ)
ኢትዪጵያዊው ሄኖክ (ሄኖክ) የታል መጽሀፍህ
በገዛ ሀገርህ ላይ ይነበብ ቃልህ (ቃልህ)
በእኔ'ና አንተ ባህል በወገህ በወጌ
እንዳላጣ እኔስ ፈራው እራሴን ፈልጌ
ምግባሬ ከጠፋኝ የማንነት ውርሴ
ባዶ ነኝ ሳላውቅ እኔ ባዳ ነኝ ለራሴ
ይቅር በለን (ይቅር ይቅር በለን)
ይቅር ይቅር በለን (ይቅር ይቅር በለን)
ይቅር በለን (ይቅር ይቅር በለን)
ዛሬም አለን በኖህ ዘመን (ዳግም በሎጥ ዘመን)
በስራዋ ክፋት ሞት ሲፈረድባት
አለም ጠፍታ ነበር ፍል ውሀ ዘንቦባት
በምህረት ቃልኪዳን በቀስተዳመና
ስለ ኖህ ተረፈች አለም እንደገና
ይቅር በለን (ይቅር ይቅር በለን)
ይቅር ይቅር በለን (ይቅር ይቅር በለን)
ይቅር በለን (ይቅር ይቅር በለን)
ዛሬም አለን በኖህ ዘመን (ዳግም በሎጥ ዘመን)
ገሞራና ሰዶም (ሰዶም) እሳት እንዳልበላቸዉ
ዳግም በምድር ላይ ማን ነው የሰራቸው (ዛሬ የሰራቸዉ)
ነፍሴ ሆይ ሰዶምን (አትይ) አትያት ዞረሽ
የጨው ሃውልት ሆኖ እንዳይቀር ገላሽ(ገላሽ)
ሰው ይባላል እንዴ ሰው ያለስብእና
ላይሰሙት ሲጮህ ያድራል የስንቱ ህሊና
ፍጥጡር ከዘነጋ ማን እንደፈጠረው
ፈርቶ በራሱ ላይ ነው ላይኖር የሚኖረው
ይቅር በለን (ይቅር ይቅር በለን)
ይቅር ይቅር በለን (ይቅር ይቅር በለን)
ይቅር በለን (ይቅር ይቅር በለን)
ዛሬም አለን በኖህ ዘመን (ዳግም በሎጥ ዘመን)
ይቅር በለን (ይቅር ይቅር በለን)
ይቅር ይቅር በለን (ይቅር ይቅር በለን)
ይቅር በለን (ይቅር ይቅር በለን)
ዛሬም አለን በኖህ ዘመን (ዳግም በሎጥ ዘመን)
ይቅር ይቅር በለን
ይቅር ይቅር በለን
ይቅር ይቅር በለን
ዳግም በሎጥ ዘመን
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri