Kishore Kumar Hits

Jacky Gosee - Kedamawit şarkı sözleri

Sanatçı: Jacky Gosee

albüm: Balambaras


በማያልቀው ፍቅርሽ ነግሰሽ በልቤ ሞገስ ደርቤ
ሁሌም አዲስ ነሽ ለኔ ቃላት ማጣልሽ በቁም ነገርሽ
ታምር አርጎ ፈጥሮት ያንቺን ሰውነት
ይሄው እኔም ኖራለሁ አብሬሽ በምድር ገነት
አብሬሽ በምድር ገነት በፍቅር በውብ ሰገነት
አክብሬሽ ሆነሽ ኩራቴ ቀዳማዊት ነሽ እመቤቴ
ተደላድዬ የህይወት ቤቴ ባንቺው ቅንነት ሰላሙ በዝቶ
ከራስሽ በላይ ከራስሽ በላይ ለኔ ማሰብሽ ይታያል ጎልቶ
ችዬ ማልከፍለው ያንቺን ውለታ የለኝም አቅሙ ልክ እንደናቴ
ባርኮ ሰጥቶኛል ወጌ ማዕረጌ የኔ ስጦታ ቀዳማዊቴ
ቀዳማዊቴ ነሽ ቀዳማዊቴ የምሳሳልሽ አዎ ልክ እንደናቴ
ግርማ ሞገሴ ነሽ ግርማ ሞገሴ የምሳሳልሽ ልክ እንደ ነፍሴ
በማያልቀው ፍቅርሽ ነግሰሽ በልቤ ሞገስ ደርቤ
ሁሌም አዲስ ነሽ ለኔ ቃላት ማጣልሽ በቁም ነገርሽ
ታምር አርጎ ፈጥሮት ያንቺን ሰውነት
ይሄው እኔም ኖራለሁ አብሬሽ በምድር ገነት
በፍቅር በውብ ሰገነት
አክብሬሽ ሆነሽ ኩራቴ ቀዳማዊት ነሽ እመቤቴ
የነፍሴን ዜማ ያንደበቴን ቃል በሚያውቀው ልብሽ እያስተዋልሽኝ
ሁለመናየን ሁለመናየን ፍቅር አጥምቀሽ ዳግም ሰራሽኝ
እንደ ወይን ሐረግ ፍቅራችን ፀድቆ የገነት አምሳል ባረግሽው ቤቴ
ሰረገላው ላይ ከብረሽ ኑሪልኝ የልቤ ንግስት ቀዳማዊቴ
ቀዳማዊቴ ነሽ ቀዳማዊቴ የምሳሳልሽ አዎ ልክ እንደናቴ
ግርማ ሞገሴ ነሽ ግርማ ሞገሴ የምሳሳልሽ ልክ እንደ ነፍሴ

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar