Kishore Kumar Hits

Tibebu Workyie - Zim şarkı sözleri

Sanatçı: Tibebu Workyie

albüm: Alamarrm (Ethiopian Contemporary Music)


ባላወድስሽ ጧት ማታ
አይክፋሽ በኔ ዝምታ
አፌ ባይነግርሽ ልሳኔ
ታማኝ አፍቃሪሽ ነኝ እኔ
ባላወድስሽ ጧት ማታ
አይክፋሽ በኔ ዝምታ
አፌ ባይነግርሽ ልሳኔ
ታማኝ አፍቃሪሽ ነኝ እኔ
አልወድም ከንቱ ዉዳሴ ለልብ ያልሆነ መኃላ
በአፌ ወደድኩሽ ባልልሽ ፍቅሬን አትይዉ በሌላ
ፊት ለፊት ሳይሽ ባገኝሽ የምለዉ ነገር አጣለዉ
ስለይሽ ቤቴ ገብቼ ለፍቅርሽ አነባለዉ
(ዝም) ዝም ማለት (ዝም) ይቀናኛል
(ዝም) እንዴት ላርቀዉ (ዝም) ለምዶብኛል
(ዝም) ግራ አይግባሽ (ዝም) ሁኔታዬ
(ዝም) ትርጉም አለዉ (ዝም) ዝምታዬ
ባላወድስሽ ጧት ማታ
አይክፋሽ በኔ ዝምታ
አፌ ባይነግርሽ ልሳኔ
ታማኝ አፍቃሪሽ ነኝ እኔ
ባላወድስሽ ጧት ማታ
አይክፋሽ በኔ ዝምታ
አፌ ባይነግርሽ ልሳኔ
ታማኝ አፍቃሪሽ ነኝ እኔ
ተናግሮ ሰዉን ማሳመን አልችም ድሮም አቃለዉ
አብሮኝ ያደገዉ ተፈጥሮ ሆኖብኝ ዝም እላለዉ
እኔም ፈልጌዉ አይደለም ምን ላርገዉ የኔን ዝምታ
ፍቅሬን መረዳት ካሰነሽ ስሚዉ የልቤን ትርታ
(ዝም) በአንደቴ (ዝም) ባልነግርሽም
(ዝም) ከልቤ ነዉ (ዝም) ሳፈቅርሽ
(ዝም) ግራ አይግባሽ (ዝም) ሁኔታዬ
(ዝም) የፍቅር ነዉ (ዝም) ዝምታዬ
(ዝም) ዝም ማለት (ዝም) ይቀናኛል
(ዝም) እንዴት ላርቀዉ (ዝም) ለምዶብኛል
(ዝም) ግራ አይግባሽ (ዝም) ሁኔታዬ
(ዝም) ትርጉም አለዉ (ዝም) ዝምታዬ
ዝም ዝም ዝም ዝም ዝም ዝም
ዝም ዝም ዝም ዝም ዝም ዝም

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar