Kishore Kumar Hits

Tibebu Workyie - Gebagne Ahungena şarkı sözleri

Sanatçı: Tibebu Workyie

albüm: Alamarrm (Ethiopian Contemporary Music)


ገባኝ አሁን ገና ገባኝ አሁን ገና
ከሰው ጋር ለመኖር አቋራጭ ጎዳና
ማስመሰል መሆኑን እያደረ ገና
ማስመሰል መሆኑን እያደረ ገና
ገባኝ አሁን ገና ገባኝ አሁን ገና
ከሰው ጋር ለመኖር አቋራጭ ጎዳና
ማስመሰል መሆኑን እያደረ ገና
ማስመሰል መሆኑን እያደረ ገና
አንድን መፅሐፍ ውስጡን አይተው ሳያጠኑ
ቢፈርዱበት ያሳዝናል በሽፋኑ
ለማስመሰል አልችል ብዬ ስላቃተኝ
ሌላ አደለም የኔው ጠላት እራሴው ነኝ
ከሰው ጋር አብሬ ለመኖር
ለጊዜው ማስመሰል ባልችልም
እራሴን እስከማውቀው ድረስ
ያን ያህል ክፉም አደለሁም
ግልፅነት እራሴን መሆኔ
ቢለየኝ ሃዘኔ ያበቃል
ብከፋም በሰው ቂም አልይዝም
የልቤን ፈጣሪ ግን ያውቃል
ሁሉንም በሱ ላይ ትቻለው
ማስመሰል አልችልም አውቃለው
ልነጠል ግዴለም ልታገስ
እውነቱን እስከሚያውቁት ድረስ
ሁሉንም በሱ ላይ ትቻለው
ማስመሰል አልችልም አውቃለው
ልነጠል ግዴለም ልታገስ
እውነቱን እስከሚያውቁት ድረስ
ሁሉንም በሱ ላይ ትቻለው
ማስመሰል አልችልም አውቃለው
ልነጠል ግዴለም ልታገስ
እውነቱን እስከሚያውቁት ድረስ
ገባኝ አሁን ገና ገባኝ አሁን ገና
ከሰው ጋር ለመኖር አቋራጭ ጎዳና ግና
ማስመሰል መሆኑን እያደረ ገና
ማስመሰል መሆኑን እያደረ ገና
ገባኝ አሁን ገና ገባኝ አሁን ገና
ከሰው ጋር ለመኖር አቋራጭ ጎዳና
ማስመሰል መሆኑን እያደረ ገና
ማስመሰል መሆኑን እያደረ ገና
ሰው ቀርቤ ሰው ሲርቀኝ ሳላስበው
ብዙ ጊዜ ግልጽነቴን እረግማለው
የገባኝን ከመናገር ስለማላርፍ
ክፉ ሆኖ ስሜ ገብቷል በሰዎች አፍ
ብቻውን ይኖር ዘንድ በምድር
የሰው ልጅ እንዴት ይቻለዋል
ጓዳዬን ዘግቼ አልቀመጥ
ይህ ልቤ ሰው ይናፍቀዋል
ሰው ራቀኝ ተቀየመኝ ብዬ
በፀፀት እራሴን አልቀጣም
ግድ የለም እምነቴ በሱ ነው
አንድ ቀን ቢጤዬን አላጣም
ሁሉንም በሱ ላይ ትቻለው
ማስመሰል አልችልም አውቃለው
ልነጠል ግዴለም ልታገስ
እውነቱን እስከሚያውቁት ድረስ
ሁሉንም በሱ ላይ ትቻለው
ማስመሰል አልችልም አውቃለው
ልነጠል ግዴለም ልታገስ
እውነቱን እስከሚያውቁት ድረስ

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar