እንደ እህል እንደ ውሃ ይርባል ይጠማል
ጨዋታሽስ ይቅር ኩርፊያሽ ይናፈቃል
እንኳን ከአጠገቤ ከጎኔ ርቀሽ
አላውቅም ጠግቤ ዓይኔ ስር ሆነሽ
እንደ እህል እንደ ውሃ ይርባል ይጠማል
ጨዋታሽስ ይቅር ኩርፊያሽ ይናፈቃል
እንኳን ከአጠገቤ ከጎኔ ርቀሽ
አላውቅም ጠግቤ ዓይኔ ስር ሆነሽ
ያ ጣፋጭ ፍቅራችን ተስፋችን ያበጀው
ባካል ብንለያይ ታትሟል አንፍቀው
ቀን ባይል ብንለይ ሆኖብን እህል ውሀ
ትዝታሽ አለልኝ ህይወቴን ማቆያ
ከአውራ ጎዳናው ከተጓዝንበት ካለፍንበት
ሳልፍ ሳገድም እንባዬ ይፈሳል እንደ ዘበት
አይጠፋም ካይኔ ቁም ነገር ለዛው ያለሽ ውበት
አንዳች ቀን የለም ያንን ውብ ጊዜ ምረሳበት
ካይኔ አጠፊም ሁሌ ሁሌ
ካይኔ አጠፊም
ካይኔ አጠፊም ሁሌ ሁሌ
አንቺ አካሌ
ካይኔ አጠፊም ሁሌ ሁሌ
ካይኔ አጠፊም
ካይኔ አጠፊም ሁሌ ሁሌ
አንቺ አካሌ
እንደ እህል እንደ ውሀ ይርባል ይጠማል
ጨዋታሽስ ይቅር ኩርፊያሽ ይናፈቃል
እንኳን ካጠገቤ ከጎኔ ርቀሽ
አላውቅም ጠግቤ ዓይኔ ስር ሆነሽ
እልፍ ቢሆን ጓዙ የትዝታሽ ዓይነት
ቢበረታ ውግያው ቢታገለኝ ናፍቆት
እንደ ማህረቧ እንደ እናቴ ሙዳይ
አስቀምጬሻለው በልቤ ሳላሳይ
ከአውራ ጎዳናው ከተጓዝንበት ካለፍንበት
ሳልፍ ሳገድም እምባዬ ይፈሳል እንደ ዘበት
አይጠፋም ካይኔ ቁም ነገር ለዛው ያለሽ ውበት
አንዳች ቀን የለም ያንን ውብ ጊዜ ምረሳበት
ካይኔ አጠፊም ሁሌ ሁሌ
ካይኔ አጠፊም
ካይኔ አጠፊም ሁሌ ሁሌ
አንቺ አካሌ
ከይኔ አጠፊም ሁሌ ሁሌ
ካይኔ አጠፊም
ካይኔ አጠፊም ሁሌ ሁሌ
አንቺ አካሌ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri