Kishore Kumar Hits

Gizachew Teshome - Alemye şarkı sözleri

Sanatçı: Gizachew Teshome

albüm: Yehuna (2001-2008)


በተትረፈረፈ ሞልቶ በፈሰሰ
ላንቺ ና ለኑሮ እንዲያው ስም አነሰ
በተሰጠሽ ፀጋ ከላይ ባገኘሽው
ጨምረሽ ጨምረሽ ፍቅሬን አባባሽው
አብሺው አብሺው አባብሺው
በጭራሽ በጭራሽ አትቀንሺው
መጨመር ነው እንጂ በየለቱ
ልብ ለማይገዛው ለኔ አይነቱ
ወደ ኅላ የለም ወደ ኃላ
ስበሽ ካስገባሽኝ በኃላ
ወደ ኅላ የለም ወደ ኃላ
የምን ማፈግፈግ ነው ወደ ኃላ
ወደ ኅላ የለም ወደ ኃላ
ከገቡማ አንዴ ከሜዳው
ወደ ኅላ የለም ወደ ኃላ
ወደፊት ነው ከሀሳብ መሄጃው.
በይማ በይ አብሺው
ያምራል ጭፈራ አብሺው
ባንቺማ ላይ አብሺው
በይማ በይ አብሺው
ደርሰሽ ተቃጥለሽ አብሺው
ዝም አትበይኝ አብሺው
የለቱ ገበያ ስሰማ እየናረ
እሱን ሳብሰለስል ቀልቤ ርቆኝ ቀረ
አሁን ግን ሲገባኝ የጥያቄው መልሱ
ወዝወዝ ማለት ነው ካ'ሳብ ሲመለሱ
አይደለም እንዴ
አይደለም እንዴ
ዋሸው እንዴ?
አይደለም እንዴ
ባሳብ ተገናኝተው ክንፍ ያሉ ለታ
እንዴት ያስደስታል ካገር ልጅ ጨዋታ
ወጋ ወጋ አድርጎ በቀላል በቀላል
ከሚወዱት ጋር መጫወት ደስ ይላል
አይደለም እንዴ
አይደለም እንዴ
ዋሸው እንዴ?
አይደለም እንዴ
አርማሽ ነፃነት ነው ምድርሽ አረንጓዴ
ድማም ያገሬ ልጅ አይደለሽም እንዴ
ውበት ደም ግባትሽ ባገር ልብስሽ ፈክቶ
አስቸገረኝ እንጂ ጥርጣሬሽ በዝቶ
አይደለም እንዴ
አይደለም እንዴ
ዋሸው እንዴ?
አይደለም እንዴ
ማናት አትበይኝ ስልኬ ሲጮኸ ድንገት
ሀናም ጎረቤቴ ሳራም እህቴ ናት
እንደ ራስሽ እይው ግድ የለም አንዳንዴ
ያጎቴ ልጅ ስትይ አምንሽ የለም እንዴ
አይደለም እንዴ
አይደለም እንዴ
ዋሸው እንዴ?
አይደለም እንዴ
እንዲ ነው አንዳንዴ!
ወደ ኅላ የለም ወደ ኃላ
ስበሽ ካስገባሽኝ በኃላ
በኔ እንዳታሳብቢ በኃላ
ወደ ኃላ የለም ወደ ኃላ
ወደፊት ነው እንጂ በርትቶ
ወደ ኃላ የለም ወደ ኃላ
ታሞ እንጂ አይሞትም ሰው ፈርቶ
ወደ ኃላ አይልም ወደ ኃላ
በይማ በይ (አብሺው)
ይለያል ዛሬ (አብሺው)
የኔስ ጉዳይ(አብሺው)
በይማ በይ(አብሺው)
ደርሰሽ ነካክተሽ(አብሺው)
ዝም አትበይ(አብሺው)
መዝነን ካየነው ሁሉንም በፍቅር
ካዘን ሳቅ ይወጣል ከቀልድ ቁም ነገር
መጫወት ነው እንጂ ፍቅር ይዞ ብልጫ
ለፀባይ ነው እንጂ ለፀብ የለው ዋንጫ
አይደለም እንዴ
አይደለም እንዴ
ዋሸው እንዴ?
አይደለም እንዴ
ካዋልሺኝ ጋር ሳልውል ካሰብሺኝ ሳላድር
ምን ይሉታል ያንቺን ደርሶ መጠራጠር
ችሎታ ሳያንስሽ ባመል በጠባይ
በገዛ ሜዳሽ ላይ ነጥብ አትጣይ
አይደለም እንዴ
አይደለም እንዴ
ዋሸው እንዴ?
አይደለም እንዴ
ገሀድ ወጣ ብለሽ የቤቴ ገመና
ቂም አትዥም በኔ የገባሽ ነሽና
ካጠፋውም ይኸው ማሪኝ በይ በሰው ፊት
ትርፉ መአቀብ ነው ካንቺ ጋር መጣላት
አይደለም እንዴ?
አይደለም እንዴ?
ዋሸው እንዴ?
አይደለም እንዴ
ያፀናንን ፍቅር ያቆየንን አይቶ
ማየት የተመኘ ከሀሳብ ጭንቀት ወቶ
እንደኛ በፍቅር እንዲያ በሂወቱ
ሁሉም ይሞክረው ገብቶ በየቤቱ
አይደለም እንዴ?
አይደለም እንዴ?
ዋሸው እንዴ?
አይደለም እንዴ?
እንዲ ነው አንዳንዴ።

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar