እምባዬን ሁሉ ባንቺ ሃዘን አፈሰስኩኝ
በዚህ አለም መፈጠሬን አማረርኩኝ
እምባዬ ፈሶ አልፎልኛል
ያንቺ እንባ ግን ይቀጥላል
መጀመርያ አንቺን ሳገኝ ተደስቼ
እውነት መስሎኝ ልቤን ሰጠሁሽ ተዝናንቼ
ከሴቶቹ ሁሉ አብልጬ
አንቺን ወደድኩ ተሳስቼ
ከሴቶቹ ሁሉ አብልጬ
አንቺን ወደድኩ ተሳስቼ
ቁጭ ካልኩበት አስነስተሽ ተዋውቀሽኝ
ጠብቀኝ ብለሽ ሳላስበው ተለየሺኝ
ካንቺ ወዲያ ሴት አላምንም
ለማግኘትም አልሞክርም
ካንቺ ወዲያ ሴት አላምንም
ለማግኘትም አልሞክርም
እምባዬን ሁሉ ባንቺ ሀዘን አፈሰስኩኝ
በዚህ አለም መፈጠሬን አማረርኩኝ
እምባዬ ፈሶ አልፎልኛል
ያንቺ እምባ ግን ይቀጥላል
እምባዬ ፈሶ አልፎልኛል
ያንቺ እምባ ግን ይቀጥላል
ያለፈ አልፏል ካሁን ወዲ አንገናኝም
እንደ ድሮው የማከብርሽ አይመስለኝም
ይቅርታ ብትይ አልቀበልም
ካንቺ ወዲያ ሴት አላምንም
ይቅርታ ብትይ አልቀበልም
ካንቺ ወዲያ ሴት አላምንም
ካንቺ ወዲያ ሴት አላምንም
ካንቺ ወዲያ ሴት አላምንም
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri