Kishore Kumar Hits

Ephrem Tamiru - Kir Alegne şarkı sözleri

Sanatçı: Ephrem Tamiru

albüm: Yehese Ken Balefe, Vol. 10


ግር አለኝ ነገርሽ
ጠፍተሽኝ በአመልሽ
እንቆቆልሽ መስሎ ጨዋታሽ ከብዶኛል
ሁኔታሽ በሙሉ ተለውጦብኛል
ቅር አለኝ ነገርሽ
ጠፍተሽኝ በአመልሽ
እንቆቆልሽ መስሎ ጨዋታሽ ከብዶኛል
ሁኔታሽ በሙሉ ተለውጦብኛል
የደበቅኩት ሁሉ ይወጣል ፊቴ ላይ
ነገር መያዝ አልችል እኔ ካንገት በላይ
በልቡ እየኖረ የሰው ልጅ ቅሬታ
ነገር አይደብቅም አይን እንደ በሽታ
ሰው አርሶ ካጨደ ዳመናውም ዳምኖ
ለፍቶ ያገኘውን ያጣል ወይ ለምኖ
አሳድጌው ነበር ፍቅርሽን ኮትኩቼ
አልታደልኩም እንጂ ለመብላት አንኩቼ
ግር አለኝ ነገርሽ
ጠፍተሽኝ በአመልሽ
እንቆቆልሽ መስሎ ጨዋታሽ ከብዶኛል
ሁኔታሽ በሙሉ ተለውጦብኛል
ቅር አለኝ ነገርሽ
ጠፍተሽኝ በአመልሽ
እንቆቆልሽ መስሎ ጨዋታሽ ከብዶኛል
ሁኔታሽ በሙሉ ተለውጦብኛል
በጣዕምሽ በለዛሽ በአመልሽ ስኩራራ
ምነው መምረር ያዘ የፍቅርሽ ሸንኮራ
ልቤ ሲጠብቅሽ በራፉን ከፋፍቶ
ሳይመለስ ቀረ ያ ፈገግታሽ ጠፍቶ
ሰው አርሶ ካጨደ ዳመናውም ዳምኖ
ለፍቶ ያገኘውን ያጣል ወይ ለምኖ
አሳድጌው ነበር ፍቅርሽን ኮትኩቼ
አልታደልኩም እንጂ ለመብላት አንኩቼ

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar