ቂም አልይዝም ባንቺ አስቀየምሽኝ ብዬ
ይቅር እልሻለዉ ሁሉን ነገር ችዬ
አልጨክንብሽም አልቀርም አምርሬ
እቀበልሻለዉ ተመለሺ ፍቅሬ
ተይልኝ ተይልኝ የልብሽን ሀዘን እርግፍ አድሪጊልኝ
ተይልኝ ተይልኝ የልብሽን ሀዘን እርግፍ አድሪጊልኝ
ሀዘኔን ትቻለዉ በደልም ጨርሳኝ
ይቅር ብዬ አሜን አንቺን ከሚነሳኝ
ከፍተሸ ጊቢ በሬን ከፍተሸ እንደወጣሽ
ጥፋትሽን ልሸከም ጨርሼ ከማጣሽ
ናፈቀኝ ፈገግታሽ የጨዋታሽ ለዛ
መጣ በዙሪያዬ የፍቅርሽ መዓዛ
ዛሬም እንደፊቱ እንኑር በጋራ
እጠብቅሻለዉ ከይቅርታ ጋራ
ቂም አልይዝም ባንቺ አስቀየምሽኝ ብዬ
ይቅር እልሻለዉ ሁሉን ነገር ችዬ
አልጨክንብሽም አልቀርም አምርሬ
እቀበልሻለዉ ተመለሺ ፍቅሬ
ተይልኝ ተይልኝ የልብሽን ሀዘን እርግፍ አድሪጊልኝ
ተይልኝ ተይልኝ የልብሽን ሀዘን እርግፍ አድሪጊልኝ
አጥፍቻለዉ እያልሽ መፀፀት አይጉዳሽ
እንዴት እቀራለሁ አንቺን ሳልረዳሽ
ፍቅር አሰራት እንጂ አይሻም ጠበቃ
ያለፈዉ አለፈ ተመለሺ በቃ
አንቺስ መች ፀፀትሽ አራቀሽ ከጎኔ
ብዙ ነዉ ከፍቅርሽ የቀረብኝ እኔ
መሳሳት ያለ ነዉ አታርጊዉ እንግዳ
ይልቅ ፍጠኝልኝ ብዙ እንዳልጐዳ
አንቺስ መች ፀፀትሽ አራቀሽ ከጎኔ
ብዙ ነዉ ከፍቅርሽ የቀረብኝ እኔ
መሳሳት ያለ ነዉ አታርጊዉ እንግዳ
ይልቅ ፍጠኝልኝ ባክሽ ብዙ እንዳልጐዳ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri