Kishore Kumar Hits

Ephrem Tamiru - Yemejemeriyay şarkı sözleri

Sanatçı: Ephrem Tamiru

albüm: Huala Endaykocheshe (Ethiopian Contemporary Music)


አየሁት አየሁት መውደድን አየሁት
አየሁት አየሁት ሁሉንም አየሁት
እንደአንቺ የሚስማማኝ የለም ያገኘሁት
ሁሉንም አየሁት
አየሁት አየሁት መውደድን አየሁት
አየሁት አየሁት ሁሉንም አየሁት
እንደአንቺ የሚስማማኝ የለም ያገኘሁት
ሁሉንም አየሁት
በስንት አጀብ መሀል በሰው ተከብቤ
የአንቺን ጨዋታ ነው የሚራበው ልቤ
በምቹ አልጋዬ ላይ እያጣሁ እንቅልፍ
ከአንቺ ጎጆ ታዛ ያምረኛል ማረፍ
ፍቅርን አንድ ሁለቴ ሞክሬው ነበረ
ግን አንቺን ለመርሳት ውስጤ ተቸገረ
ግን አንቺን ለመርሳት ውስጤ ተቸገረ
ማን እንደሷ እላለው መልሼ እንደገና
መውደድ እና ማፍቀር አንድ አይደሉምና
መውደድ እና ማፍቀር አንድ አይደሉምና
አሳይተሽኛል የፍቅርን ልዩ ጣዕም
ለኔም ላንቺም የሚሆን ከየትም አይመጣም
አባባል አይደለም ተረዳሁት አሁን
ለካ ሰው አይረሳም የመጀመሪያውን
ናፈቅሽኝ ገላዬ ናፈቅሽኝ ገላዬ
ናፈቅሽኝ ገላዬ የመጀመሪያዬ
ናፈቅሽኝ ገላዬ ናፈቅሽኝ ገላዬ
ናፈቅሽኝ ገላዬ የመጀመሪያዬ
ናፈቅሽኝ ገላዬ ናፈቅሽኝ ገላዬ
ናፈቅሽኝ ገላዬ የመጀመሪያዬ
ናፈቅሽኝ ገላዬ ናፈቅሽኝ ገላዬ
ናፈቅሽኝ ገላዬ የመጀመሪያዬ
አየሁት አየሁት መውደድን አየሁት
አየሁት አየሁት ሁሉንም አየሁት
እንደአንቺ የሚስማማኝ የለም ያገኘሁት
ሁሉንም አየሁት
አየሁት አየሁት መውደድን አየሁት
አየሁት አየሁት ሁሉንም አየሁት
እንደአንቺ የሚስማማኝ የለም ያገኘሁት
ሁሉንም አየሁት
ሰው ማፍቀር አንዴ ነው በህይወት ዘመን
ከራስ በላይ ወዶ ቤዛ እስከመሆን
እኔም ከአሁን ወዲያ ሌላ መቼ ያምረኛል
ፍቅር ብሎ ጣጣ በአንቺ ወቶልኛል
ፍቅርን በጠዋቱ ያስተማርሽው ልቤ
እንዳለምድ አረገኝ ሌላ ሰው ቀርቤ
እንዳለምድ አረገኝ ሌላ ሰው ቀርቤ
በስራ በእረፍቴ ስጫወት ሳወጋ
ሀሳቤ በመሀል ይጓዛል ከአንቺ ጋራ
ሀሳቤ በመሀል ይጓዛል ከአንቺ ጋራ
አንቺን አጣው እንጂ መፅናኛ አግንቻለው
ትዝታሽን ወዳጅ አርጌ እኖራለው
ከስንት አንድ ሰው ነው በኪዳን ተሳስሮ
ከመጀመሪያው ጋር የሚዘልቀው አብሮ
ነይ ነይ ገላዬ ነይ ነይ ገላዬ
ነይ ነይ ገላዬ የመጀመሪያዬ
ነይ ነይ ገላዬ ነይ ነይ ገላዬ
ነይ ነይ ገላዬ የመጀመሪያዬ
ነይ ነይ ገላዬ ነይ ነይ ገላዬ
ነይ ነይ ገላዬ የመጀመሪያዬ
ነይ ነይ ገላዬ ነይ ነይ ገላዬ
ነይ ነይ ገላዬ የመጀመሪያዬ

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar