አርፎ ባ'ንድ አበባ መች ታውቅና ኑሮ
ሁሉን ትቀስማለች እንደ ቢራቢሮ
እንደ ንብ አክብሬ ሰቅዬላት ቀፎ
ደጅ አዳሪው ልቧ አይቀመጥ አርፎ
እንደ ቢራቢሮ ሁሉን አትቅሰሚ
እኔ እበቃሻለሁ ተይ ፍቅሬ ስሚ
እንደ ቢራቢሮ ሁሉን አትቅሰሚ
እኔ እበቃሻለሁ ተይ ፍቅሬ ስሚ
ታምኜ ለኪዳን ልቤ አድሮ ለቃሉ
አንቺ ልትበሪ ክንፍ አወጣሽ አሉ
ካንድ 'ማያሳድር ክፉ አመል አለሽ
ለኔም እንዳይተርፈኝ ያንቺ መዘዝሽ
የንብ ዞሮ መቅሠም ወለላ ቢሰጥም
ካንቺ መዘዝ እንጂ ማር አይቆረጥም
እንደ ቢራቢሮ ሁሉን አትቅሰሚ
እኔ እበቃሻለሁ ተይ ፍቅሬ ስሚ
እንደ ቢራቢሮ ሁሉን አትቅሰሚ
እኔ እበቃሻለሁ ተይ ፍቅሬ ስሚ
ታምኜ ለኪዳን ልቤ አድሮ ለቃሉ
አንቺ ልትበሪ ክንፍ አወጣሽ አሉ
እንደ ንብ አክብሬ ሰቅዬላት ቀፎ
ደጅ አዳሪው ልቧ አይቀመጥ አርፎ
እንደ ቢራቢሮ ሁሉን አትቅሰሚ
እኔ እበቃሻለሁ ተይ ፍቅሬ ስሚ
እንደ ቢራቢሮ ሁሉን አትቅሰሚ
እኔ እበቃሻለሁ ተይ ፍቅሬ ስሚ
እንደ ቢራቢሮ ሁሉን አትቅሰሚ
እኔ እበቃሻለሁ ተይ ፍቅሬ ስሚ
ስሚ
ስሚ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri