Kishore Kumar Hits

Teddy Afro - Abugida şarkı sözleri

Sanatçı: Teddy Afro

albüm: Abugida


አቦጊዳ ብዬ ፊደል አስቆጥሬ
የፍቅርን ትርጉም ለልቤ አስተምሬ
ይዤሽ ባኮፋዳ እንደ ቆሎ ተማሪ
አቦጊዳ ልበል የፍቅሩ ጅማሪ
ሀ-ግዕዝ ሁ-ካልዕ ሂ-ሳልስ ሃ-ራብዕ ሄ-ሃምስ ሆ-ሳብእ
ሀ-ግዕዝ ሁ-ካልዕ ሂ-ሳልስ ሃ-ራብዕ ሄ-ሃምስ ሆ-ሳብእ
የወደድኳት በማለዳ
በልጅነት በአቦጊዳ
የፍቅር ቃል መቁጠሪያዬ
የመጀመሪያዬ
አቦጊዳ
ሀ የኔታ ለመምህሩ
አቦጊዳን ሲያስተምሩ
ማልዳ ወግታኝ ከፊደል ጣት
አሁን ከየት ላምጣት?
አቦጊዳ (አቦጊዳ)
አ-ቦ-ጊ-ዳ-ሄ-ው-ዞ አቦጊዳ
አቦጊዳ ኦዳ
ሁሌ የጀማሪ እዳ
አ-ቦ-ጊ-ዳ-ሄ-ው-ዞ አቦጊዳ
አቦጊዳ ኦዳ
ሁሌ የጀማሪ እዳ
ምሎላታል በፊደሉ
ላይታጠፍ ልቤ ቃሉ
ይኑር እንጂ ሲከልሳት
'ሀ' ን እንዴት ሊረሳት
አቡጊዳ
ገና ልጅ ነኝ ብላቴና
ስለፍቅር መች አውቅና
አስጠናችው ልቤን ወስዳ
የፍቅር አቦጊዳ
አቦጊዳ (አቦጊዳ)
አ-ቦ-ጊ-ዳ-ሄ-ው-ዞ አቦጊዳ
አቦጊዳ ኦዳ
ሁሌ የጀማሪ እዳ

ሀ-ግዕዝ ሁ-ካልዕ ሂ-ሳልስ ሃ-ራብዕ ሄ-ሃምስ ህ-ሳድስ ሆ-ሳብእ
መልዕክተ ዮሐንስ ሐዋርያ ወልደዘብድዮስ (ሀ-ግዕዝ ሁ-ካልዕ ሂ-ሳልስ)
ንዜንወክሙ በእንተ ውዕቱ (ሃ-ራብዕ ሄ-ሃምስ ህ-ሳድስ)
መልዕክተ ዮሐንስ (ሆ-ሳብእ)
የወደድኳት በማለዳ (ሀ-ግዕዝ ሁ-ካልዕ ሂ-ሳልስ)
በልጅነት በአቦጊዳ (ሃ-ራብዕ ሄ-ሃምስ)
የፍቅር ቃል መቁጠሪያዬ (ህ-ሳድስ ሆ-ሳብእ)
የመጀመሪያዬ (ሀ-ግዕዝ ሁ-ካልዕ)
አቡጊዳ (ሂ-ሳልስ ሃ-ራብዕ ሄ-ሃምስ)
ሀ የኔታ ለመምህሩ (ህ-ሳድስ ሆ-ሳብእ)
አቦጊዳን ሲያስተምሩ (ሀ-ግዕዝ ሁ-ካልዕ)
ማልዳ ወግታኝ ከፊደል ጣት (ሂ-ሳልስ ሃ-ራብዕ ሄ-ሃምስ)
አሁን ከየት ላምጣት (ህ-ሳድስ ሆ-ሳብእ)
አቦጊዳ
(ሀ-ግዕዝ ሁ-ካልዕ ሂ-ሳልስ ሃ-ራብእ ሄ-ሃምስ ህ-ሳድስ ሆ-ሳብእ)
(ሀ-ግዕዝ)

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar