Kishore Kumar Hits

Teddy Afro - Lemi Leleleh (Affe) şarkı sözleri

Sanatçı: Teddy Afro

albüm: Yasteseryal


ኡኡ ባልል ባፌ ውጣ ከተራራ
ድምፁ ሳይገጫጭ አንዱ ካንዱ ጋራ
ኡኡ ሳትል አፌ ዛሬ በሰዓቱ
'ጅብ ከሄደ ውሻ' ይሆናል ጩኸቱ
ኡኡታዬ ላይሰማ ያኔ ኤ-ኤ
ነይ ብላትም አስኪነቃ ልሣኔ ኤ-ኤ
እሪታዬ ቃሌ ላይሰማ
ኡ ሳልል ኡ ባልል ኡ ሳልል ካፌ
አፌ አፌ ሰሚ ለሌለህ ያኔማ
አፌ አፌ ሰሚ ለሌለህ ያኔማ
ዘመን ያገነነው ጅብ ቆሟል ከበሬ (ኡኡታዬ)
አፌ እንዳታስበላኝ ባለመናገሬ (ኡኡታዬ)
እያየህ ስትወጣ ልትጫወት በእሳት (ኡኡታዬ)
ምን ያረጋል አፌ ካለፈ ብትወቅሳት (ኡኡታዬ)
አይቶ በዝምታ በስተመጨረሻ (ኡኡታዬ)
ቢጮህ ምን ያረጋል ጅብ ከሄደ ውሻ (ኡኡታዬ)
ኦ-ኦሆሆ-ሆ ተናገራት አፌ
ኦ-ኦሆሆ-ሆ ሳይመጣ ደመና
ኦ-ኦሆሆ-ሆ ጅቡ ከበራፍህ
ኦ-ኦሆሆ-ሆ ላይ ነውና ሃሃ-ሃ
ኤ-ኤ ኤ-ሄ-ሄ
ኡኡታዬ ላይሰማ ያኔ ኤ-ኤ
ነይ በል አሁን አስኪነቃ ልሳኔ ኤ-ኤ
እሪታዬ ቃሌ ላይሰማ
ኡ ሳልል ኡ ባልል ኡ ሳልል ቢያልፍብኝ
አፌ አፌ ሰሚ ለሌለህ ያኔማ
አፌ አፌ ሰሚ ለሌለህ ያኔማ
ቀለበትሽ ከኔ ልብሽ ከሌላ ሰው (ኡኡታዬ)
ይህ አለመታመን ቤቱን ካፈረሰው (ኡኡታዬ)
ለሦስቱ ጉልቻ ገባሁ ስል ከቤቴ (ኡኡታዬ)
ነፍሴ እንዳትጠራ በቀለበት ጣቴ (ኡኡታዬ)
አፌ በዝምታ ብታልፋት በንቀት (ኡኡታዬ)
ከነባለቤት ነው የጥሪው ወረቀት (ኡኡታዬ)
ኦ-ኦሆሆ-ሆ ተናገራት አፌ
ኦ-ኦሆሆ-ሆ ሳይመጣ ደመና
ኦ-ኦሆሆ-ሆ ጅቡ ከበራፍህ
ኦ-ኦሆሆ-ሆ ላይ ነውና ሃሃ-ሃ
ኤ-ኤ ኤ-ሄ-ሄ
ኡኡታዬ ላይሰማ ያኔ ኤ-ኤ
ነይ በል አሁን አስኪነቃ ልሣኔ ኤ-ኤ
እሪታዬ ቃሌ ላይሰማ
ኡ ሳልል ኡ ባልል ኡ ሳልል ቢያልፍብኝ
አፌ አፌ ሰሚ ለሌለህ ያኔማ
አፌ አፌ ሰሚ ለሌለህ ያኔማ
ኡኡታ ተይ መኝታ የሌላ
ኡኡታ ተይ መኝታ የሌላ
ኡኡታዬ ላይሰማ ያኔ ኤ-ኤ
ነይ በል አሁን አስኪነቃ ልሣኔ ኤ-ኤ
እሪታዬ ቃሌ ላይሰማ
ኡ ሳልል ኡ ባልል ኡ ሳልል ካፌ
አፌ አፌ ሰሚ ለሌለው ያኔማ
አፌ አፌ ሰሚ ለሌለው ያኔማ
ኡኡታ ተይ መኝታ የሌላ
ኡኡታ ተይ መኝታ የሌላ
ኡኡታ ተይ መኝታ የሌላ
ኡኡታ ተይ መኝታ

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar