Teddy Afro - Habdahlak şarkı sözleri
Sanatçı:
Teddy Afro
albüm: Yasteseryal
ዳሕላክ ላይ ልስራ ቤቴን
ቁርጥ ሆኗል መለየቴ
ነጠለኝ ክፉ ዘመን
ከምወዳት ባለቤቴ
ቀን ብሎ እስክንገናኝ
ያረግሽልኝ የእምነት ቃልሽ
አይወጣም ለዘላለም
ከጣቴ ላይ ቀለበትሽ
♪
ካለሁበት ቦታ
ሲደርሰኝ ደብዳቤ
ይረበሽ ጀመረ
ቅር እያለው ልቤ
ወይ አልመጣ ነገር
አቋርጬ ዱሩን
ዝሆኖች ተጣልተው
ሰበሩት ድንበሩን
ዳሕላክ ላይ ልስራ ቤቴን
ቁርጥ ሆኗል መለየቴ
ነጠለኝ ክፉ ዘመን
ከምወዳት ባለቤቴ
ቀን ብሎ እስክንገናኝ
ያረግሽልኝ የእምነት ቃልሽ
አይወጣም ለዘላለም
ከጣቴ ላይ ቀለበትሽ
በዝሆን ፀብ ሲጎዳ ሳሩ
ዝም አይልም ያያል እግዜሩ
አይሻለው በቀለበቴ
እሰኪያበቃኝ እኔን ለቤቴ
እንዳልከዳሽ ቃል አለብኝ
እንዳልከዳሽ
እንዳልከዳሽ ቃል አለብኝ
እንዳልከዳሽ
እንዳልከዳሽ ቃል አለብኝ
እንዳልከዳሽ
እንዳልከዳሽ ቃል አለብኝ
እንዳልከዳሽ
♪
ዳሕላክ ላይ ልስራ ቤቴን
ቁርጥ ሆኗል መለየቴ
ነጠለኝ ክፉ ዘመን
ከምወዳት ባለቤቴ
ቀን ብሎ እስክንገናኝ
ያረግሽልኝ የእምነት ቃልሽ
አይወጣም ለዘላለም
ከጣቴ ላይ ቀለበትሽ
♪
ዳሕላክ ደሴቱ ላይ
አይቼ አንድ መርከብ
በማዕበል ተይዛ
ሲያስጨንቃት ወጀብ
እንስት ህፃን ይዛ
ቆማ ከመርከቡ
ለአምላክ ብትነግረው
ፀጥ አለ ወጀቡ
በይ እንዲህ ነው ህልሜ ሲፈታ
ለህፃን ነፍስ ይራራል ጌታ
አትሙት ብሎት ያለ ሀጥያቱ
መዳን ሆነ ለመርከቢቱ
ቂም ማወቁ ልቡን አይረዳም
እስከሚደርስ ፍሬያችን ለአዳም
ካስተማርሽው ፍቅርን በጊዜ
አይሻለው ወይ በሱ ጊዜ
እንዳልከዳሽ ቃል አለብኝ
እንዳልከዳሽ
እንዳልከዳሽ ቃል አለብኝ
እንዳልከዳሽ
እንዳልከዳሽ ቃል አለብኝ
እንዳልከዳሽ
እንዳልከዳሽ ቃል አለብኝ
እንዳልከዳሽ
እንዳልከዳሽ ቃል አለብኝ
እንዳልከዳሽ
እንዳልከዳሽ ቃል አለብኝ
እንዳልከዳሽ
እንዳልከዳሽ ቃል አለብኝ
እንዳልከዳሽ
እንዳልከዳሽ ቃል አለብኝ
እንዳልከዳሽ
እንዳልከዳሽ ቃል አለብኝ
እንዳልከዳሽ
እንዳልከዳሽ ቃል አለብኝ
እንዳልከዳሽ
እንዳልከዳሽ ቃል አለብኝ
እንዳልከዳሽ
እንዳልከዳሽ ቃል አለብኝ
እንዳልከዳሽ
እንዳልከዳሽ ቃል አለብኝ
እንዳልመጣ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri