ከአካሌ ሳይጠፋ ሰምበሬ ከአካሌ
ከአካሌ ሳይጠፋ ሰምበሬ ከአካሌ
አምና ፍቅር ጎድቶኝ ከአካል ከልቤ ላይ ሳይጠፋ ሰምበሬ
ከአካሌ ሳይጠፋ ሰምበሬ ከአካሌ
ደግሞ ሌላ አገኘኝ አዲስ ገላ ለብሶ እዩትና ዛሬ
ከአካሌ ሳይጠፋ ሰምበሬ ከአካሌ
ሰው መውደድ ዕርሜ ነው
እያልኩኝ ፎክሬ
ያንን ጉራ ሁሉ (ያን ጉራ)
ገላ ናደው ዛሬ
ከአካሌ ሳይጠፋ ሰምበሬ ከአካሌ
አምና ፍቅር ጎድቶኝ ከአካል ከልቤ ላይ ሳይጠፋ ሰምበሬ
ከአካሌ ሳይጠፋ ሰምበሬ ከአካሌ
ደግሞ ሌላ አገኘኝ አዲስ ገላ ለብሶ እዩትና ዛሬ
ከአካሌ ሳይጠፋ ሰምበሬ ከአካሌ
አልደግምም ቃሌ ነው
እያልኩኝ ፎክሬ
ያንን ጉራ ሁሉ (ያን ጉራ)
ቀን አራደው ዛሬ
ያን ጉራ ሁላ ጉራ ሁላ
ያን ጉራ ሁላ ትታ ነፍሴ
ወኔዬ ከዳኝ ወንድነቴ
ወድቆ ጨነቀኝ ኩራቴ
ያን ጉራ ሁላ ጉራ ሁላ
ያን ጉራ ሁላ ትታ ነፍሴ
ወኔዬ ከዳኝ ወንድነቴ
ወድቆ ጨነቀኝ ኩራቴ
♪
የቅብጥ ሃሳብ ጤዛ ነው ሲነጋ ረጋፊ
ወትሮም በአፍ ቃል ይፈጥናል ቀድሞ ተሸናፊ
ላያድን ቃል ብቻ
ምን ያደርጋል ዛቻ
ጉራ ብቻ
ያን ጉራ ሁላ ጉራ ሁላ
ያን ጉራ ሁላ ትታ ነፍሴ
ወኔዬ ከዳኝ ወንድነቴ
ወድቆ ጨነቀኝ ኩራቴ
ስማ! ስማ! ስማ!
♪
ስልቻ ቀልቀሎ ቀልቀሎ ስልቻ ጉራ ብቻ
ቦታ ቢለዋወጥ ወጥ ላያጥም ጉልቻ ጉራ ብቻ
ልቤ ዛሬም ወደህ ልትሆን መተረቻ ጉራ ብቻ
ታዲያ ምን አመጣው ያንን ሁሉ ዛቻ ጉራ ነው ከአካሌ
ከአካሌ ሳይጠፋ ሰምበሬ ከአካሌ (ከአካል ከአካሌ)
ከአካሌ ሳይጠፋ ሰምበሬ ከአካሌ
ታላቅና ታናሽ ምላስ እና ሰምበር ጉራ ብቻ
ያስገምታል ስጋ ሞቶ ለሚቀበር ጉራ ብቻ
ወርቅ የዘጋ ሳጥን ቁልፍ የሌለው መፍቻ ጉራ ብቻ
ምን ያደርጋል ወድቀው አለሁ ማለት ብቻ ጉራ ነው ከአካሌ
ከአካሌ ሳይጠፋ ሰምበሬ ከአካሌ (ከአካል ከአካሌ)
ከአካሌ ሳይጠፋ ሰምበሬ ከአካሌ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri