Kishore Kumar Hits

Madingo Afework - Tzita şarkı sözleri

Sanatçı: Madingo Afework

albüm: Aydergem ( Ethiopian Contemporary Music)


አግኝቶ ላያገኝ ወይ ጠቅሞ ላይጠቅመዉ
ሰው ለምን ይኖራል ትዝታ ሲያደክመው
አግኝቶ ላያገኝ ወይ ጠቅሞ ላይጠቅመዉ
ሰው ለምን ይኖራል ትዝታ ሲያደክመው
ትርጉሙ ምንድን ነው ምንድን ነው ትዝታ
ምንድን ነው ሰው ማሰብ ምንድን ነው ትዝታ
እባክህ ተው የማይሉት የሁሉም ሰው ጌታ
ይሄው ሰው ይኖራል በትዝታ ሰበብ
ይሄው ሰው ይኖራል በትዝታ ሰበብ
የኋሊት ሲጋልብ ትላንት በማሰብ
ሰው እንዴት ባለፈው በትላንት ይኖራል
ሰው እንዴት ባለፈው በትላንት ይኖራል
ዛሬን በእጁ ይዞ ለነገው ይሰራል
ዛሬን በእጁ ይዞ ለነገው ይሰራል
ልበል ትዝታ ደርሳ በሽታዬ
ከትጋርደኝ ልይበት የነገው ተሰፋዬ
ባይጠፋ አሻራው ትዝታው ቢነፍስም
ባለፈ አመት ዝናብ ዛሬ አይታረስም
በትዝታ ሰበብ ላለፈው ሲጨነቅ
ስንት ሰው አለፈ ከአምላክ ሳይታረቅ
እገነባለሁ እንጂ ድካሙ ቢያመኝም
ለፈረሰው ቤቴ ሳለቅስ አልገኝም
ያለፈን ላይቀይር በከንቱ ይለፋል
ያለፈን ላይቀይር በከንቱ ይለፋል
መቼም ሰው ደፋር ነው አምላኩን ይጋፋል
ትንሽ እልፍ ሲሉን እልፍ አየተገኘን
ትንሽ እልፍ ሲሉን እልፍ አየተገኘን
ደሃ ነው በልቡ ሞቱን የተመኘ
ነነ
ለምን በትዝታ ኑሮዬን እገፋለሁ
ለምን በትዝታ ኑሮዬን እገፋለሁ
ኑሮዬን እገፋለሁ
ለምን በትዝታ ኑሮዬን እገፋለሁ
ኑሮዬን እገፋለሁ
ማጣትም እንዳለ ለማግኘት ጊዜ አለው
ማጣትም እንዳለ ለማግኘት ጊዜ አለው
አቅም አለኝ ብሎ የሰው ልጅ ቢሰፍርም
አቅም አለኝ ብሎ የሰው ልጅ ቢሰፍርም
የሰው ልጅ ቢሰፍርም
አቅም አለኝ ብሎ የሰው ልጅ ቢሰፍርም
የሰው ልጅ ቢሰፍርም
ታሰበ አልታሰበ ከልኩ አያልፍም
ታሰበ አልታሰበ ከልኩ አያልፍም
ታሰበ አልታሰበ ከልኩ አያልፍም
ታሰበ አልታሰበ ከልኩ አያልፍም
ታሰበ አልታሰበ ከልኩ አያልፍም
ታሰበ አልታሰበ ከልኩ አያልፍም
አግኝቶ ላያገኝ ወይ ጠቅሞ ላይጠቅመዉ
ሰው ለምን ይኖራል ትዝታ ሲያደክመው
አግኝቶ ላያገኝ ወይ ጠቅሞ ላይጠቅመዉ
ሰው ለምን ይኖራል ትዝታ ሲያደክመው

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar