ተንገበገበልሽ አረረልሽ ሆዴ
አትራቂኝ በኔ ሞት አይብዛ መንደዴ
ያስታርቀን መውደዴ
ልመናዬን ስሚኝ ይቅርታሽ ይድረሰኝ
ጥፋቴን ለመርሳት እኔ አቅም አነሰኝ
ልቤ እየወቀሰኝ
ከትዝታሽ ንዳድ አልዳነም አንጀቴ
አንቺን ካጣሁ ወዲህ ተጨንቋል ስሜቴ
አልበላም አልጠጣም እምቢ እያለኝ ሆዴ
ለይግባኝ ሳይታይ ሊቀር ነው ወይ ፍርዴ
የእድሜዬን ጧት ማታ በትካዜ ገፋሁ
አጣሁት ሰላሜን አንቺን ስላስከፋሁ
ያለውን ችያለሁ መጪው ካልከበደኝ
ፀልይልኝ ፍቅርሽ እንዳያሳብደኝ
ላንቺ ይብላኝ እንጂ አልል አልተመቸኝ
ላንቺ ይብላኝ እንጂ አልል አልተመቸኝ
እወዳታለሁ ማለት አይሰለቸኝ
እወዳታለሁ ማለት አይሰለቸኝ
ተራዬን ብነሳ ልበር እንደገዴ
ብመርጠው መራቁን በልጥራኝ መንገዴ
ስትሄጂ ቢከፋኝ ስሞታ አላሰማ
ተለየሽኝ ብዬ ዛሬ አንቺን አላማ
ክፉሽን አውርቼ አልኖርም ሲቆጨኝ
ቅናት ነው ጠላቴ እኔ የሚያነጫንጨኝ
ዳር እስከ ዳር ብዞር ልክሽን አላገኝ
ልርሳሽ ብል መንፈሴ ሰውም አያረገኝ
እንባዬን ባፈሰው አፍ ላይ ደቀኑበት
የኔ ቃላት ናቸው እኔን የቀኑበት
አይኔን እየረሳሁ በዛፍ በቅጠሉ
ተብሰልሳይ አርጎኛል ካንቺ መነጠሉ
ትካዜን አጥምደው ምንም ቢፈዙበት
ያዩበታል እንጂ ወፍን አይዙበት
እባክሽ እባክሽ ታረቂኝ ተይ አታስጨንቂኝ
እባክሽ እባክሽ ታረቂኝ ተይ አታስጨንቂኝ
ልቦናሽ ከኔ አካል ሊርቅ መወሰኑ
ጠፍቶብሽ ይሆን ወይ የመቻል ወሰኑ
አንድም ፀፅቶኛል ለሱ በይኝ ይቅር
አይለምደውም ጥፋት ሰው ሲቀጣው ፍቅር
ልቦናሽ ከኔ አካል ሊርቅ መወሰኑ
ጠፍቶብሽ ይሆን ወይ የመቻል ወሰኑ
አንድም ፀፅቶኛል ለሱ በይኝ ይቅር
አይለምደውም ጥፋት ሰው ሲቀጣው ፍቅር
እሄሄሄ እሄሄሄ ነይ
ምነው በትዝታ ሁሌ እንደምመኝሽ
ከጉጉቴ መረብ ተቀምጠሽ ባገኝሽ
እኔ አዳኝ አይደለሁ አላልም በጫካ
ምንሽሬ እንባ ነው ምንም ባይሳካ
ብዙ ማልቀስ በአዳም ባይለመድ እንኳን
ባንቺ ሀዘን ልቤ ላይ አስጥያለሁ ድንኳን
ብትሰባብረኝም ምድር ለአራት ታጥፋ
አብረን እንኑርና እስኪ አብሬሽ ልጥፋ
ቀራኒዮም ይስማ ጎሎጎታም ይወቅ
አይረዳን ምረቱ እኛ ሳንታረቅ
ባይፃፍም ሰዓት ላለም መጨረሻ
ቀን ማጣት ምፃት ነው ላንቺ መመለሻ
እባክሽ እባክሽ ታረቂኝ ተይ አታስጨንቂኝ
እባክሽ እባክሽ ታረቂኝ ተይ አታስጨንቂኝ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri