የእውንት መንገድ ተጀመረ
በአምላክ ፈቃድ በከበረ
አዲስ ምዕራፍ አዲስ ደስታ
ተገመደ ላይፈታ
እንደ ፀሀይ የፀና ከላይ
ያልበቀለ ከእሾህ ከአረም ላይ
የተዘራ ከእውንት ፈሬ
የሚያባብል ውዴ ፍቅሬ
የማይደበዝዝ የማያቋርጥ
ከዛሬው በላይ ነገ ሚጣፍጥ ሆ
ሁሌም ሙሽራ ሁሌም አበባ
የማይጠውልግ በረከት ይግባ ሆ
እንዳርከው ሱፍ እንደ ቬሎዋ
እንዳጎርስካት እንደጉርሻዋ ሆ
ከፍ ከፍ ይበል ሁሌም ፍቅራቹ
እንደተነሳው እንደፅዋቹ ኦ
የደስታ ቀን ነው የምን ዝምታ
ይደብላለቅ ምሬት ይምታ
ምስክሮቹ ይሙሽሮቹ
ወዳጅ ቤተሰብ እስኪ እንያቹ
ሙሽራው (ወይን አበባው)
ሙሽራዬ (ወይን አበባዬ)
ሚዜዎቿ (አብሮ አደጎቿ)
ሚዜዎቹ (ጓደኞቹ)
አድምቁላቸው (አጅቧችው)
በእልልታ ሆታ (በሰርጋችው)
ለእናት ለአባትም (ወግ ማዕረግ ነው)
የተቀደሰ (ልዩ ቀን ነው)
ገና መች ገና (ተነካና)
ቸብ ቸብ አርጉት (ተነሱና)
በልቶ ጠጥቶ (መጫወት ነው)
በሀገር ባህሌ (ሰርግ አለም ነው)
ዎ ዎ ሆይሆይ
(ልጄን በምን አየሀት ተመኘሀት)
ውብ ከፀሀይ የታደለች ናት
(ልጄን በምን አየሀት ተመኘሀት)
የተቆጠበች የጨዋ ልጅ ናት
(ልጄን በምን አየሀት ተመኘሀት)
ያውም የወንዜ ያግሬ ልጅ ናት
(ልጄን በምን አየሀት ተመኘሀት)
በብዙ ምክንያት ተሸነፍኩላት
(ልጄን በምን አየሀት ተመኘሀት)
(እንኳን አየሃት አገባሃት)
(አገባሃት አስገባሃት)
(አገባሃት አስገባሃት)
(አገባሃት አስገባሃት)
(አገባሃት አስገባሃት)
(ልጄን በምን አየሽው ተመኘሽው)
በጓደኞቹም የሚወደድ ነው
(ልጄን በምን አየሽው ተመኘሽው)
በቁም ነገሩም የሚለይ ነው
(ልጄን በምን አየሽው ተመኘሽው)
ስራውን ወዳድ ጥሮ አዳሪ ነው
(ልጄን በምን አየሽው ተመኘሽው)
እናት አባቱን ስው አክባሪ
(ልጄን በምን አየሽው ተመኘሽው)
(እንኳን አየሽው አገባሽው)
(አገባሽው አስገባሽው)
(አገባሽው አስገባሽው)
(አገባሽው አስገባሽው)
(አገባሽው አስገባሽው)
የማይደበዝዝ የማያቋርጥ
ከዛሬው በላይ ነገ ሚጣፍጥ ሆ
ሁሌም ሙሽራ ሁሌም አበባ
የማይጠውልግ በረከት ይግባ ሆ
እንዳርከው ሱፍ እንደ ቬሎዋ
እንዳጎርስካት እንደጉርሻዋ ሆ
ከፍ ከፍ ይበል ሁሌም ፍቅራቹ
እንደተነሳው እንደፅዋቹ ኦ
ሙሽራው (ወይን አበባው)
ሙሽራዬ (ወይን አበባዬ)
ሚዜዎቿ (አብሮ አደጎቿ)
ሚዜዎቹ (ጓደኞቹ)
አድምቁላቸው (አጅቧችው)
በእልልታ ሆታ (በሰርጋችው)
ለእናት ለአባትም (ወግ ማዕረግ ነው)
የተቀደሰ ልዩ (ቀን ነው)
ገና መች ገና (ተነካና)
ቸብ ቸብ አርጉት (ተነሱና)
በልቶ ጠጥቶ (መጫወት ነው)
በሀገር ባህሌ (ሰርግ አለም ነው)
ዎ ዎ ሆይሆይ
(እሷን በምን አየሃት ተመኘሃት)
ዋዛ ፈዛዛ የማያጓጓት
(እሷን በምን አየሃት ተመኘሃት)
አረማመዷ የተቃናላት
(እሷን በምን አየሃት ተመኘሃት)
በምኞት ብቻ መች አስቅረዋት
(እሷን በምን አየሃት ተመኘሃት)
የዘላለሜ የኔ አደረኳት
(እሷን በምን አየሃት ተመኘሃት)
(እንኳን አየሃት አገባሃት)
(አገባሃት አስገባሃት)
(አገባሃት አስገባሃት)
(አገባሃት አስገባሃት)
(አገባሃት አስገባሃት)
(እሱን በምን አየሃት ተመኘሽው)
ምኞቴም ህልሜም የሱ አይነት ሰው
(እሱን በምን አየሃት ተመኘሽው)
ለሴት ልጅ ክብር ትልቅ ቦታ አለው
(እሱን በምን አየሃት ተመኘሽው)
ተንከባካቢ ፍቅር አዋቂ
(እሱን በምን አየሃት ተመኘሽው)
ለቃሉ ታማኝ ብረት መዝጊያ
(እሱን በምን አየሃት ተመኘሽው)
(እንኳን አየሽው አገባሽው)
(አገባሽው አስገባሽው)
(አገባሽው አስገባሽው)
(አገባሽው አስገባሽው)
(አገባሽው አስገባሽው)
(አገባሃት አስገባሃት)
(አገባሃት አስገባሃት)
(አገባሃት አስገባሃት)
(አገባሃት አስገባሃት)
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri