ቀኑ ይህ ቀን ነበር አስታውሰዋለው
በእርጋታ ጉዞዬ ሁሉን እየቃኘው
ቆንጆ ልቤን ሰርቃው
መንገድ ቆሜ ቀረው
ያንን አጋጣሚ እንዴት እረሳዋለው
እስቲ ልመልስሽ በትዝታ ይዤሽ
አይንሽን እያየሁ አይኗ አይኔን እያየው
እንደው በአጋጣሚ ባይሆን የእድል ነገር
አንቺስ ባታገኚኝ የማን ትሆኝ ነበር
ሀገሩን ውብ ሞልቶት
አንቺን ወዶ ቀልቤ
ስንቴ አሰበበት በልብሽ በልቤ
እሺ እንደሆን ቃልሽ መቼ ጠፋው ልቤ
መቼም አትረሽውም ሁሉን ነገር ሁሌ
ፊትሽ ቃል አጥቼ
መርበትበት ማፈሬ
መሳቅሽ ለደስታ
መፍራቴ ለፍቅር
አልገረመሽም ወይ
ሆኖ ስናይ ዛሬ
የኔ... ውድ
የኔው... ነሽ
እኔም የምንጊዜሽ
የኔ ውድ የኔው ነሽ
እኔም የምንጊዜሽ
ሁሌ አብሬሽ ብሆን
ሁል ጊዜ ብለይሽ
የማልፈታሽ ቅኔ ሰምና ወርቅ ነሽ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri