Kishore Kumar Hits

Abinet Agonafir - Kal Yibekal şarkı sözleri

Sanatçı: Abinet Agonafir

albüm: Astaraky


ነይ እንዳልል እኔ
ምን ይዘህ ይለኛል ጎኔ
ነይ እንዳልል እኔ
ቢከፋሽ እጄን ከምኔ
ሁኚ ሰላም ብቻ ይደርሳል
ከተሳሰብን ይሰምራል
ሁኚ ሰላም ብቻ ይደርሳል
ከተዋደድን ይሆናል
እሱ እንደው ሁሉን ያውቃል
ቃል ይበቃል፣ አልወጣም ከቃልሽ ከሀሳብሽ
ለኔ የተውሽውን ተስፋ ጥለሽ ላልተውሽ
ቀጣኝ ይሄ አቅሜ ስጓጓልሽ
ነይ ብዬ እንዳልጠራሽ ቅርቤ ሆነሽ
ቢዘገይም እንኳን ርቆ ሀሳቤ
አልከዳሽም ያልኩሽ፣ ነው ከልቤ
በማተቤ አልወጣም ከቃልሽ፣ ከሀሳብሽ
ለኔ የተውሽውን ተስፋ ጥለሽ፣ ላልተውሽ
የለም ምፈራው እኔ በዚህ ምድር
ካላጣው ያንቺን ፍቅር
ሰበቤ በዝቶ አትሰልቺብኝ
ይሆናል አይዞህ በዪኝ
ነይ እንዳልል እኔ
ምን ይዘህ ይለኛል ጎኔ
ነይ እንዳልል እኔ
ቢከፋሽ እጄን ከምኔ
ሁኚ ሰላም ብቻ ይደርሳል
ከተሳሰብን ይሰምራል
ሁኚ ሰላም ብቻ ይደርሳል
ከተዋደድን ይሆናል
እሱ እንደው ሁሉን ያውቃል
ቃል ይበቃል፣አልወጣም ከቃልሽ ከሀሳብሽ
ለኔ የተውሽውን ተስፋ ጥለሽ ላልተውሽ
ተመልከችው ሰርቀሽ ያይኔን ውሀ
ነፍሴ ስትፈልግሽ ድሀ ድሀ
አላየሽልኝም የኔን ነገር
ለፍርድ አይመችም ተይው ይቅር
የኔ ፍቅር፣ አልወጣም ከቃልሽ ከሀሳብሽ
ለኔ የተውሽውን ተስፋ ጥለሽ ላልተውሽ
የለም ምፈራው እኔ በዚህ ምድር
ካላጣው ያንቺን ፍቅር
ሰበቤ በዝቶ አትሰልቺብኝ
ይሆናል አይዞህ በዪኝ

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar