ኧረ አስታራቂ የለም ወይ
ሃይ የሚለን ሰው ገላጋይ
ቀናት አለፉ ተኮራርፈን
ምን ነክቶአችሁ ነው የሚል አጥተን
ኧረ አስታራቂ የለም ወይ
ሃይ የሚለን ሰው ገላጋይ
ቀናት አለፉ ተኮራርፈን
ምን ነክቶአችሁ ነው የሚል አጥተን
አኩርፈሽኝ ስውል ጭር ሲል እቤቱ (ደስ አይለኝም)
ከሰቀቀን ካልዳንኩ ካምናው ከትላንቱ (ደስ አይለኝም)
ዝምታ ሲውጠኝ ምን እንደምል ሳጣ (ደስ አይለኝም)
አንቺን አገኝ ብዬ እኔ እራሴን ሳጣ (ደስ አይለኝም)
አፅናነተሽኝ አይዞህ ብለሽ ሆዴን ባዶ አስቀርተሸ (ደስ አይለኝም)
ለአንገት የሚከብደው ራስ እንደሌለም አንቺ እያወቅሽ (እንደገና)
ፍቅር የተራበው ልቤን በእቅፎችሽ አስጠልዬ (እንደገና)
እንደልጅነት ትዝታ እንደ አዲስ ባንቺ በቅዬ (እንደገና)
አልቆምም ሸንጎ እኔስ ችዬ
አልሄድ ጨክኜ አይ እዳዬ
ለማን ልተውሽ ብዬሽ በርቺ
ዘመደ ብዙ አይደለሽም አንቺ
ገላጋይ የለም አስታራቂ
አንተም አንቺም ተይ የሚል አዋቂ
እሳት የሚያበርድ የሚያጠፋ
አንድ የልብ ወዳጅ እንዴት ሸምጋይ ይጥፋ
ኧረ አስታራቂ የለም ወይ
ሃይ የሚለን ሰው ገላጋይ
ቀናት አለፉ ተኮራርፈን
ምን ነክቶአችሁ ነው የሚል አጥተን
ኧረ አስታራቂ የለም ወይ
ሃይ የሚለን ሰው ገላጋይ
ቀናት አለፉ ተኮራርፈን
ምን ነክቶአችሁ ነው የሚል አጥተን
ገልጠሸ ገመናዬን አንብበሽ ስትረሺው (ደስ አይለኝም)
የልቤን ጎዶሎ አንቺው ካልሞላሽው (ደስ አይለኝም)
ሳቅ ጨዋታው ጠፍቶ አለች አለ ብቻ (ደስ አይለኝም)
በአይን መጠባበቅ አብረን ለየብቻ (ደስ አይለኝም)
እያየሽ አስተውለሽ እያወቅሽኝ ብለሽ ችላ (እንደገና)
አንድ ስንዝር ሳንራራቅ በዝምታችን ከለላ (እንደገና)
ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ዳግም እንዳይሆን ቋንቋችን (እንደገና)
ይለኮስ ይብራ ሻማችን ርቆ ከንፋስ ፍቅራችን (እንደገና)
አልቆምም ሸንጎ እኔስ ችዬ
አልሄድ ጨክኜ አይ እዳዬ
ለማን ልተውሽ ብዬሽ በርቺ
ዘመደ ብዙ አይደለሽም አንቺ
ገላጋይ የለም አስታራቂ
አንተም አንቺም ተይ የሚል አዋቂ
እሳት የሚያበርድ የሚያጠፋ
አንድ የልብ ወዳጅ እንዴት ሸምጋይ ይጥፋ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri