ተመስገን ተመስገን ተመስገን
ይመስገን ይመስገን ይመስገን
ከዘመን ዘመን አሸጋግሮ
አሮጌው በአዲስ ተቀይሮ
ለዚ ያደረሰን ፈጣሪያችን
ይክበር ይመስገን
♪
እለምን ሰላም ጤናዬን
ነግሬው ነበረ የሆድ ሚስጥሬን
የልቤ ደረሰ አዎን ደረሰ ጌታ ተመስገን
ፀሎቴ ደረሰ አዎን ደረሰ አምላክ ተመስገን
♪
ኦሆሆይ የመከራዬ ቀንበር ተሰብሯል
እህ የልቤ ሀዘን ባንተ ተቀብሯል
እህ ዘመድ ሲርቀኝ የሆንከኝ ወገን
አሄ ለዚ ያበቃኸኝ ክበር ተመስገን
ክብር ጌታ ተመስገን ክብር አምላክ ተመስገን
ክብር ጌታ ተመስገን ክብር አምላክ ተመስገን
♪
እንባዬንም ጠርጎ ሀዘኔን አርቆ
አምላክ ነው የረዳኝ የኔን ጉዳት አውቆ
የአለም መዳኒት ደጋፊና አለኝታ
ልዘምር ለክብርህ ላረከው ውለታ
ታምር ነው ያንተ ነገር ድንቅ ነው ያንተ ስራ
ስጦታህ አይነገር ውለታህ አይወራ
ታምር ነው ያንተ ነገር ድንቅ ነው ያንተ ስራ
ወሮታህ አይከፈል ውለታህ አይወራ
♪
ኦሆ ጬኸቴን ሰምተህ ችላ ያላልከኝ
እኽ ተድላና ደስታ ያደልከኝ
አሀ ከዙፋንህ ላይ ያደላደልከኝ
አኼን አምላኬ አንተ ነህ ከፍ ያደረከኝ
ክብር ጌታ ተመስገን ክብር አምላክ ተመስገን
ጌታ ሆይ ተመስገን ክብር አምላክ ተመስገን
ድንቅ ተአምር አምላክ ያንተ ስራ
ጭለማውን ገፈህ ፀሐይ የምታበራ
ምስጋናና ክብር ላንተ እንዴት ያንስሀል
ተመስገን አምላኬ ምን የከፈልሀል
ታምር ነው ያንተ ነገር ድንቅ ነው ያንተ ስራ
አለፍኩት ያን አቀበት ወጣውት ካንተጋራ
ታምር ነው ያንተ ነገር ድንቅ ነው ያንተ ስራ
አለፍኩት ያን አቀበት ወጣውት ካንተጋራ
ታምር ነው ያንተ ነገር ድንቅ ነው ያንተ ስራ
አለፍኩት ያን አቀበት ወጣውት ካንተጋራ
ተመስገን ተመስገን ተመስገን (ተመስገን)
ይመስገን ይመስገን ይመስገን (ይመስገን)
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri