በነፋሻው አየር ወጥቼ ስጓጓዝ ቆንጆን አይቼ
ጠጋ አልኩኝ ተረትቼ የረጋ አንደበቱን ሰምቼ
ያን ጣፋጭ ከንፈሩን ቀምሼ
ገባሁ ቤቴ ተመልሼ
♪
ከዛ ከራሱ አድራሻውን ጠይቄ
ወዲያው መግቢያና መውጫውን አውቄ
ባካል ባሳብ ላልለየው ወስኜ
በቃ ተጠቃለልኩለት ታምኜ
መደበቅ ተስኖኝ የልቤን ትርታ
ራሴን አስረከብኩት ባንድ ቀን እይታ
♪
በሀሳብ አጓጉሎ አድርሶ መላሹ
ገዝግዞ አደንዝዞ ገላ አካል ጨራሹ
እያለ ትዝታው በለሊት ደራሹ
ኧረ እንዴት ይመቸን አልጋና ፍራሹ
ወይ ስቃይ ለሊቱም አይነጋ አሀ አሀ በወግ አይመሽ ቀኑ
ወይ ስቃይ እንኳን ቀርቶ ሲቆይ አሄ አሄ አይጣል ሰቀቀኑ
ወይ ስቃይ የጀምር መጥለቂያው አሀ አሀ ሲድስርማ ጊዜ
ወይ ስቃይ እኔው ነኝ መስፈሪያው አሀ አሀ የሀሳብ የትካዜው
♪
ባካል በሀሳብ አትለየኝ አለሜ
ሳጣህ ጭንቀት ይከበኛል በቁሜ
ሳቁን ጨዋታውን ለምዷል ጎጆዬ
ላጣው አልሻም ሽቁጥቁጥ ቆንጆዬ
ሲቀር ተናፋቂ በሀሳብ አስጨናቂ
ይምጣልኝ የልቤ የኔ ህይወት አድማቂ
♪
ወይ ስቃይ ለሊቱም አይነጋ አሀ አሀ በወግ አይመሽ ቀኑ
ወይ ስቃይ እንኳን ቀርቶ ሲቆይ አሄ አሄ አይጣል ሰቀቀኑ
ወይ ስቃይ የጀምር መጥለቂያው አሀ አሀ ሲድስርማ ጊዜው
ወይ ስቃይ እኔው ነኝ መስፈሪያው አሄ አሄ የሀሳብ የትካዜ
ወይ ስቃይ ወይ ስቃይ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri