ይዳኝ ይዳኘኝ ያዬ
ይፍረደህኝ ያዬ
ይዳኘኝ ያዬ
ይዳኝ
ወዶ የጋየ
ይዳኝ ይዳኘኝ ያዬ
ይፍረደህኝ ያዬ
ይዳኘኝ ያዬ
ይዳኝ
ወዶ የጋየ
♪
እንደው የቷ ጉብል ትማርከው ልቡን
እንደው ስንቱ ዝናር ይዞረው ወገቡን
እንደው ስንቱ ኒሻን ይበቃው ደረቱን
ያሰኛል እንደ ሞኝ የዚያ ልጅ ውበቱ
ያሰኛል እንደ ሞኝ የዚያ ልጅ ውበቱ
ምን ትኮራ እናቱ ያቺ ልበ ቀና
ምን ትኮራ እናቱ ያቺ ልበ ቀና
አንድ እሱን ወልዳለች ለወንዶች ናሙና
ጋማ ፈረሱ ላይ በኩራት ተቀምጦ
ጋማ ፈረሱ ላይ በኩራት ተቀምጦ
ስንቱን አቅል ነሳ በፍቅር አስምጦ
ስንቱን አቅል ነሳ በፍቅር አስምጦ
ያጥቢያ ኮከብ መስሎ ታይቶ የተሰወረ
ለካስ ያይኑ ጦር ነው የተወረወረ
ለፍቅር ጨዋታስ ከቶ ማን እንደሱ
ላፍታ እንኳ ሲገልጠው ያሸብራል ጥርሱ
ይዳኝ ይዳኘኝ ያየ ወዶ የጋየ
ይዳኝ ይፍረደኝ ያየ ጸባዩን ያዬ
ይዳኝ ይዳኘኝ ያየ ወዶ የጋየ
ይዳኝ ይፍረደኝ ያየ ወዶ የጋየ
ይዳኘኝ ያዬ ጸባዩን ያዬ
ይዳኘኝ ያዬ ቁመቱን ያዬ
ይዳኘኝ ያዬ ውበቱን ያዬ
ይዳኘኝ ያዬ ደረቱን ያዬ
ይዳኘኝ ያዬ ጥርሱንም ያዬ
ይዳኘኝ ያ ዐይኑንም ያዬ
♪
ይዳኝ ይዳኘኝ ያየ
ይፍረደኝ ያየ
ይዳኘኝ ያዬ ወዶ የጋየ
ይዳኝ ይዳኘኝ ያየ
ይፍረደኝ ያየ
ይዳኘኝ ያዬ ይዳኝ ወዶ የጋየ
♪
እስኪ ልማጸናት የሌቷን ጨረቃ
ያን ጀኛ ካለበት ብታመጣው ሰርቃ
ጥርሱ ፊት አውራሪ አይኑ ደጃዝማች
ውበቱ አርበኛ ነው የፍቅር ዘማች
ውበቱ አርበኛ ነው የፍቅር ዘማች
ይሄ ዋናተኛ የፍቅር ጠላቂ
ይሄ ዋናተኛ የፍቅር ጠላቂ
ጨዋ አርጎ ፈጥሮታል ላገር አስጨናቂ
የተቆለፈውን የልቤን በራፍ
የተቆለፈውን የልቤን በራፍ
ፎክሮ ከፈተው እያለ ዘራፍ (ዘራፍ)
ፎክሮ ከፈተው እያለ ዘራፍ
ያጥቢያ ኮከብ መስሎ ታይቶ የተሰወረ
ለካስ ያይኑ ጦር ነው የተወረወረ
ለፍቅር ጨዋታስ ከቶ ማን እንደሱ
ላፍታ እንኳ ሲገልጠው ያሸብራል ጥርሱ
ሆይ ሆሆ ኦሆይ
ይዳኘኝ ያዬ ጸባዩን ያዬ
ይዳኘኝ ያዬ ውበቱን ያዬ
ይዳኘኝ ያዬ ቁመቱን ያዬ
ይዳኘኝ ያዬ ደረቱን ያዬ
ይዳኘኝ ያዬ ጥርሱንም ያዬ
ይዳኘኝ ያ ዐይኑንም ያዬ
ሆይ ሆይ
ይዳኝ ያዬ
ይፍረደህኝ ያዬ
ይዳኝ ያዬ ወዶ የጋየ
ይዳኘኝ ያዬ ውበቱን ያዬ
ይዳኘኝ ያዬ ቁመቱን ያዬ
ይዳኘኝ ያዬ ደረቱን ያዬ
ይዳኘኝ ያዬ ጥርሱንም ያዬ
ይዳኘኝ ያ ዐይኑንም ያዬ
ይዳኝ ያዬ ወዶ የጋየ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri