Hamelmal Abate - Gize Mizan şarkı sözleri
Sanatçı:
Hamelmal Abate
albüm: Gize Mizan
አወይ ጊዜ አወይ ጊዜ
አወይ ጊዜ ጊዜ ደራሽ
መንገደኝ ሁሌ ገስጋሽ
አወይ ጊዜ አወይ ጊዜ
አወይ ጊዜ ጊዜ ደራሽ
መንገደኝ ሁሉን ታጋሽ
ጊዜ ደፋር ጊዜ አይፈሬ
ጊዜ ሚዛን አይቸኩሌ
ትላንት ዛሬም ነገም ሁሌም
♪
ለተቀበረች ሀቅ ቋጥኝ የተጫናት
አራሙቻ ዉሸት አረም የሸፈናት
ቋጥኙን ፈልቅቆ አረሙን አርሞ
ያወጣት ጊዜ ነዉ ለጠበቀ ቆሞ
ለጠበቀ ቆሞ
♪
አሁን ዛሬ የሞላለት የደመቀዉ ያማረበት
ሲያድር ነገ ይረገጣል የቀን ፅዋ ሲጐልበት
በዉሎ አዳር በሂደቱ ሁሉም ነገር ይለወጣል
ጊዜ ካለ ሳይቻኰል ለእያንዳንዱ ፍርድ ይሰጣል
ጊዜ ተንታኝ ጊዜ አደራጅ
ጊዜ ዳኛ ጊዜ ፈራጅ
ጊዜ ሰፊዉ ጊዜ ታጋሽ
ምስክር ነዉ ጊዜ ነጋሽ
ጊዜ ነጋሽ ጊዜ ወቃሽ
ትላንተ ዛሬ ነገም ሁሌም
♪
አወይ ጊዜ አወይ ጊዜ
አወይ ጊዜ ጊዜ ደራሽ
መንገደኝ ሁሌ ገስጋሽ
አወይ ጊዜ አወይ ጊዜ
አወይ ጊዜ ጊዜ ደራሽ
መንገደኝ ሁሉን ታጋሽ
ጊዜ ደፋር ጊዜ አይፈሬ
ጊዜ ሚዛን አይቸኩሌ
ትላንት ዛሬም ነገም ሁሌም
♪
ዛሬ ነገን ባይወልድ እንደቆመ ቢቀር
ሐሰት በምድሪቱ በነገሰ ነበር
ይህ የአሁኑ ስራ የዛሬዉ ተገብሮ
ማን ይገልጠዉ ነበር ጊዜ ባይኖር ኖሮ
ጊዜ ባይኖር ኖሮ
♪
አያጋድል አያዛባ ህይወት ዉሉን መቼ ይስታል
የሰዉ ስራዉ ተመዝኖ ቀን ጠብቆ ይከሰታል
ጊዜ እንደሰዉ በማንነት አበላልጦ መች የዳላል
ሁሉም ፍጡር በተግባሩ እንደ ስራዉ ይታደላል
ጊዜ ገስጋሽ ጊዜ ደራሽ
ጊዜ ሚዛን ጊዜ ታጋሽ
ጊዜ ደፋር ጊዜ ደራሽ
ምስክር ነዉ ጊዜ ነቃሽ
ጊዜ ወቃሽ ጊዜ ነቃሽ
ትላንት ዛሬ ነገም ሁሌ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri