Kishore Kumar Hits

Hamelmal Abate - Fitagne şarkı sözleri

Sanatçı: Hamelmal Abate

albüm: Gize Mizan


እህል ውኃችን አለቀ በቃ ምን ይቀረናል
የማንቻቻል ሰዎች ሁነናል ተቃቅረናል
እህል ውኃችን አለቀ በቃ ምን ይቀረናል
የማንቻቻል ሰዎች ሁነናል ተቃቅረናል
በቃ ካሁን ጀምሮ የኛ ኑሮ በቃው ዘንድሮ

አቅም ጉልበቴን ሀብቴን ገብሬ
ራሴን ጎድቸ ሰላንተ ኑሬ
በአጥንቴ ቀረሁ አልቆ ስጋዬ
የማይገፋ ሆኗል ስቃዬ
ግፍህ በዝቶብኝ አንገፍግፎኛል
እንደ እግር እሳት አንገብግቦኛል
እርኩሱ መንፈስ ባንተ ተልኮ
ልቤ ውስጤ ተጨንቋል ልቤ ታውኮ
ፍታኝ በቃ ፍታኝ ፍታኝ
ፍታኝ በቃ ፍታኝ አታንገላታኝ
ፍታኝ በቃ ፍታኝ ፍታኝ
ፍታኝ በቃ ፍታኝ አታንገላታኝ

እህል ውኃችን አለቀ በቃ ምን ይቀረናል
የማንቻቻል ሰዎች ሁነናል ተቃቅረናል
እህል ውኃችን አለቀ በቃ ምን ይቀረናል
የማንቻቻል ሰዎች ሁነናል ተቃቅረናል
በቃ ካሁን ጀምሮ
የኛ ኑሮ በቃው ዘንድሮ

እንዳልናገር እየለጎምኸኝ
እንዳልራመድ እየጎተትኸኝ
እየበደልኸኝ እየታገስኩህ
ስንቴ አሳለፍሁህ ይቅር እያልኩህ
የማትለወጥ የማትሻሻል
ካለህ አይነጋም በቀን ይመሻል
ብርሃን አይታይ ሁሌ ጨለማ
አይዳምን ሰማይ ምድር አትለማ
ፍታኝ በቃ ፍታኝ ፍታኝ
ፍታኝ በቃ ፍታኝ ፍታኝ
ፍታኝ በቃ ፍታኝ ፍታኝ
ፍታኝ በቃ ፍታኝ አታንገላታኝ
ምንም ብትለኝ እኔ አይገባኝም
በቃ በምንም አታግባባኝም
ሁሉም በጊዜው ሊሆን ተፈቅዷል
ሰማንያችንም በቃ ተቀዷል
(ፍታኝ ፣ ፍታኝ)
(ፍታኝ ፣ ፍታኝ ፣ ፍታኝ)
በጭካኔ (ፍታኝ)
ስታጠቃኝ (ፍታኝ
ችዬህ ኖርሁኝ (ፍታኝ)
ዛሬ በቃኝ (ፍታኝ)
ከአቅሜ በላይ (ፍታኝ)
ታግሻለሁ (ፍታኝ)
ትዕግስቴ አልቆ (ፍታኝ) ቆርጫለሁ
ፍታኝ በቃ ፍታኝ ፍታኝ
ፍታኝ በቃ ፍታኝ አታንገላታኝ
ፍታኝ በቃ ፍታኝ ፍታኝ
ፍታኝ በቃ ፍታኝ አታንገላታኝ
ፍታኝ በቃ ፍታኝ አታንገላታኝ

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar