Kishore Kumar Hits

Hamelmal Abate - Meleyet şarkı sözleri

Sanatçı: Hamelmal Abate

albüm: Gize Mizan


ብቻህን እንዴት ብለህ የኔን ናፍቆት ትችላለህ
እኔ አልቻልም ለብቻዬ ናፍቆት ጐዳኝ ትዝታህ
ብቻህን እንዴት ብለህ የኔን ናፍቆት ትችላለህ
እኔ አልቻልም ለብቻዬ ናፍቆት ጐዳኝ ትዝታህ

መራራቅ ሰልችቶ መሮኛል
አላየህ አክስቶ አጥቁሮኛል
አንተንስ እንዴት አርጎህ ይሆን
አዉቃለዉ እንደኔ እንደምትሆን
አይበቃኝም እንዴ አይበቃኝም ወይ
እስከመቼ ድረስ ብቻዬን ልቆይ
አይበቃህም እንዴ አይበቃህም ወይ
እስከመቼ ድረስ ብቻህን ልትቆይ
ይበቃሀል ይበቃሀል
ናፍቆት ጎቶሃል
ይበቃኛል ይበቃኛል
መለየት መሮኛል

ብቻህን እንዴት ብለህ የኔን ናፍቆት ትችላለህ
እኔ አልቻልም ለብቻዬ ናፍቆት ጐዳኝ ትዝታህ
ብቻህን እንዴት ብለህ የኔን ናፍቆት ትችላለህ
እኔ አልቻልም ለብቻዬ ናፍቆት ጐዳኝ ትዝታህ

ቀን አልፎ ሲቆጠር ሳምንት
ወራቱም ሲተካ በአመት
የኔ እዚ የአንተ እዚያ መራቅ
ዳረገን ለመነፋፈቅ
አይበቃህም እንዴ አይበቃህም ወይ
እስከመቼ ድረስ ብቻህን ልትቆይ
በቃኝ ይበቃኛል በቃህ ይብቃህ እንጂ
ላግኝህ እንገናኝ ና የኔ ወዳጅ
ይበቃናል ይበቃናል
መለየት ጎድቶናል
ይበቃኛል ይበቃኛል
መለየት መሮኛል
ይበቃናል ይበቃናል
መለየት ጎድቶናል
ሰዉ መሃል መራራቅ ሲመጣ
ሀዘኑ እርምን አያስወጣ
የሞተን ሲቀብሩት ያርፉታል
ግን ያለን እንዴት ይረሱታል
ሰዉ መሃል መራራቅ ሲመጣ
ሀዘኑ እርምን አያስወጣ
የሞተን ሲቀብሩት ያርፉታል
ግን ያለን እንዴት ይረሱታል
ይበቃናል ይበቃናል
መለየት ጎድቶናል
ይበቃኛል ይበቃኛል
መለየት መሮኛል
ይበቃናል ይበቃናል
መለየት ጎድቶናል
ይበቃኛል ይበቃኛል
መለየት መሮኛል

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar