Kishore Kumar Hits

Hamelmal Abate - Kir Yelegnal şarkı sözleri

Sanatçı: Hamelmal Abate

albüm: Gize Mizan


ምነዉ ቅር ቅር ይለኛል እሳ ቅር ይለኛል
የረሳኸኝ ይመስለኛል ሰሞኑን ቅር ብሎኛል
ምነዉ ቅር ቅር ይለኛል እሳ ቅር ይለኛል
የረሳኸኝ ይመስለኛል ሰሞኑን ቅር ብሎኛል

እያጉረመረመ ትዝታ ከማዶ
እንዴት ይችል ይሆን ልቤ በአንተ ነዶ
አንተ የሌለህበት ሀሳብ እየጐዳኝ
ነበልባሉን ጥሶ ማን ሰዉ እኔን ይርዳኝ
አልቻልኩም ጨንቆኛል ፀንቷል አንተን መዉደድ
አይመልስህም ወይ የወሰደህ መንገድ
ናና ስጠባበቅህ አንተን ናፍቄ
አደራ አደራ መላ በል ለጭንቄ
ስጠባበቅህ ቆሜ ከደጅ
አደራ አደራ አትቅር ወዳጄ

ችሎ አይችልልኝ ልቤ ሀሳብ ያደካከመዉ
ሀሳብ ያደካከመዉ
ሰክኖ አይሰክንልኝ ቀልቤ ሀሳብ የበታተነዉ
ሀሳብ የበታተነዉ
የማይሸነፍ የማይረታ
ነበረ ልቤ ዛሬስ ተረታ
ያን ሰንጋ ፈረስ ኮርኩረዉና
ድረስ ከደጅ ሽምጥ ጋልብና
አሆሆሆሆሆ አሆሆሆሆ

ምነዉ ቅር ቅር ይለኛል እሳ ቅር ይለኛል
የረሳኸኝ ይመስለኛል ሰሞኑን ቅር ብሎኛል
ምነዉ ቅር ቅር ይለኛል እሳ ቅር ይለኛል
የረሳኸኝ ይመስለኛል ሰሞኑን ቅር ብሎኛል

ይመስልሃል እንጂ የሌለህ ከጐኔ
በፍቅር መንፈሴ አንተዉ ጋ ነኝ እኔ
ቀን በፀሀይ ብርሃን ለሊት በጨረቃ
ዘብ ቆማለች ነብሴ ነብስህን ጥበቃ
አስታዉስሃለዉ ቀንም ሆነ ማታ
በሃሳብ አትለየኝ ካለህበት ቦታ
ናና እስክንገናኝ በአካል በስጋ
አደራ አደራ እንዳትዘናጋ
በእዉነትህ ፅና በቃልህ እርጋ
እርዳኝ አደራ እኔም እንዳልሰጋ

ችሎ አይችልልኝ ልቤ ሀሳብ ያደካከመዉ
ሀሳብ ያደካከመዉ
ሰክኖ አይሰክንልኝ ቀልቤ ሀሳብ የበታተነዉ
ሀሳብ የበታተነዉ
የማይሸነፍ የማይረታ
ነበረ ልቤ ዛሬስ ተረታ
ያን ሰንጋ ፈረስ ኮርኩረዉና
ድረስ ከደጅ ሽምጥ ጋልብና
ሆይሆይሆይሆይሆይ

ችሎ አይችልልኝ ልቤ ሀሳብ በታተነው
ሀሳብ በታተነው
ሰክኖ አይሰክንልኝ ቀልቤ ሀሳብ ያደካከመዉ
ሀሳብ ያደካከመዉ
የማይሸነፍ የማይረታ
ነበረ ልቤ ዛሬስ ተረታ
ያን ሰንጋ ፈረስ ኮርኩረዉና
ድረስ ከደጅ ሽምጥ ጋልብና
ሆይሆይሆይሆይሆይ

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar