የፍቅር ፅዋ መቅመሻ መቅመሻ
የአንድነት ሸማ መልበሻ ምድረ ሐበሻ
የፍቅር ፅዋ መቅመሻ መቅመሻ
የአንድነት ሸማ መልበሻ ምድረ ሐበሻ
በሀሳብ መስመር መነሻ መድረሻ
ሁሌም ሐገሬን ሐገሬን ይላል ሀበሻ
አልደላ ቢለዉ ነዉ እንጁ ሐበሻ
አንጀት የለዉም መቁረጫ ሀገሩን መርሻ
የፍጥረት ሁሉ መድረሻ የአለም መነሻ
የሰዉ ልጅ ጐዳና መመላለሻ
የፍቅር ዳቦ መቁረሻ የህይወት ጉርሻ
የገነት ዉሃ መፍለቂያ የመፈወሻ
የፍቅር ፅዋ መቅመሻ
የአንድነት ሸማ መልበሻ
ምድረ ሐበሻ
አልደላ ቢለዉ ነዉ እንጁ ሐበሻ
አንጀት የለዉም መቁረጫ ሀገሩን መርሻ
የፍቅር ፅዋ መቅመሻ
የአንድነት ሸማ መልበሻ
ምድረ ሐበሻ
ለወገን ተስፋ ዘምሮ ደክሞ ተምሮ
ከባዕድ ሀገር ገብሮ ጉልበት አእምሮ
እስከመቼ ነዉ የስደት የጭንቀት ኑሮ
ሁሉም በሀገር ነዉ የሚያምረዉ ቁረጥ ዘንድሮ
እንግዲህ እንስራ ቁም ነገር
በሉ እንነሳ ለሀገር እንተባበር
እንግዲህ እንስራ ቁም ነገር
በሉ እንነሳ ለሀገር እንተባበር
የፍቅር ፅዋ መቅመሻ መቅመሻ
የአንድነት ሸማ መልበሻ ምድረ ሐበሻ
የፍቅር ፅዋ መቅመሻ መቅመሻ
የአንድነት ሸማ መልበሻ ምድረ ሐበሻ
በሀሳብ መስመር መነሻ መድረሻ
ሁሌም ሐገሬን ሐገሬን ይላል ሀበሻ
አልደላ ቢለዉ ነዉ እንጁ ሐበሻ
አንጀት የለዉም መቁረጫ ሀገሩን መርሻ
ከወዳጅ ዘመድ ከወገን መቀላቀሉን
መች ጠላዉ አብሮ መዋሉን አብሮ ማደሩን
አልሞላ ብሎ የያዘዉ ይዞት ነዉ እንጂ
ናፍቋል ሀገሩን አፈሩን የወዜ ልጅ
ባዶ እጄን እንዴት እያለ
ቀልጦ የቀረ ስንት አለ እንደዋለለ
ባዶ እጄን እንዴት እያለ
ቀልጦ የቀረ ስንት አለ እንደዋለለ
ወንድም ጨክን እህት ጨክኚ
አስበህ ወስን አንቺም ወስኚ
ወንድም ጨክን እህት ጨክኚ
አስበህ ወስን አንቺም ወስኚ
ሁል ጊዜ ለምን ሆድሽ ይባባ ሆድህ ይባባ
ከልኩ አያልፍም ሀገርሽ ጊቢ ሀገርህ ግባ
ሁል ጊዜ ለምን ሆድሽ ይባባ ሆድህ ይባባ
ከልኩ አያልፍም ሀገርሽ ጊቢ ሀገርህ ግባ
ረሃብ በሽታ ስቃይ ችግሩ
ይነቀል ይጥፋ ይዉጣ ከምድሩ
ልብልፅግና ጉዞ ጀምሩ ጉዞ ጀምሩ
ይመለስት የሐበሻ ክብሉ ሐበሻ ክብሩ
የኛ ምንላት ሐገር እንፍጠር ሐገር እንፍጠር
ከአንድ እንነሳ ሁለት እንበል ሁለት እንበል
አንድ ሁለት አንድ ሁለት
እስቲ ሶስት እንበል የመጨረሻ የመጨረሻ
ጉዞ እንጀምር ወደ ሐበሻ አገር መድረሻ
የኛ ምንላት ሐገር እንፍጠር ሐገር እንፍጠር
ከአንድ እንነሳ ሁለት እንበል ሁለት እንበል
አንድ ሁለት አንድ ሁለት
እስቲ ሶስት እንበል የመጨረሻ የመጨረሻ
ጉዞ እንጀምር ወደ ሐበሻ አገር መድረሻ
ሐገር የጋራ የሁሉ ትሁን
ይሄን ጥያቄ እንመልስ አሁን
የሐበሻ ልጆች እንገባ አነድ ላይ
ሐገራችንን በልፅጋ እንድናይ
አንበታተን በአንድነት እንቁ በአንድነት እንቁ
ከፍ ከፍ ይበል ክብር ሰንደቁ ክብር ሰንደቁ
አንበታተን በአንድነት እንቁ በአንድነት እንቁ
ከፍ ከፍ ይበል ክብር ሰንደቁ ክብር ሰንደቁ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri