አሁን አሁን ወስን አሁን
የብቻዬ የግሌ ሁን
አሁን አሁን ወስን አሁን
የብቻዬ የግሌ ሁን
ተያይተን ተፈላልገናል ተያይተን
ተዋዉቀን ተቀራርበናል ተዋዉቀን
ተናበን ተጠናንተናል ተናበን
እንግዲህ ምን ይቀረናል በቃ
አሁን አሁን ወስን አሁን
የብቻዬ የግሌ ሁን
አሁን አሁን ወስን አሁን
የብቻዬ የግሌ ሁን
♪
አንተም የኔ ሆነህ እኔም የአንተ ብቻ
ህይወቴ እንዲሰክን በሶስቱ ጉልቻ
ሁለት አካላችን አንድ ይሁን ተጣምሮ
ቃል ኪዳን እንሰር ከዛሬ ጀምሮ
በቃ ጊዜ አንግደል አናብዛ ቀጠሮ
አንድላይ እንሁን እንወስን ዘንድሮ
በቃ ጊዜ አንግደል አናብዛ ቀጠሮ
እንዳናመነታ እንወስን ዘንድሮ
በአንድ ጎጆ ጣሪያ ደምቀን አብረን ስንገባ አብረን ስንገባ
እልል እልል ይባልልን ጉሮ ወሸባ ጉሮ ወሸባ
በአንድ ጎጆ ጣሪያ ደምቀን አብረን ስንገባ አብረን ስንገባ
እልል እልል ይባልልን ጉሮ ወሸባ ጉሮ ወሸባ
አሁን አሁን አሁን አሁን
አሁን አሁን አብረን እንሁን
አሁን አሁን አሁን አሁን
አሁን አሁን አብረን እንሁን
♪
አሁን አሁን ወስን አሁን
የብቻዬ የግሌ ሁን
አሁን አሁን ወስን አሁን
የብቻዬ የግሌ ሁን
ተያይተን ተፈላልገናል ተያይተን
ተዋዉቀን ተቀራርበናል ተዋዉቀን
ተናበን ተጠናንተናል ተናበን
እንግዲህ ምን ይቀረናል በቃ
አሁን አሁን ወስን አሁን
የብቻዬ የግሌ ሁን
አሁን አሁን ወስን አሁን
የብቻዬ የግሌ ሁን
♪
ከአንድ ሁለት ሆኖ እንጂ ተዋዶ ተፋቅሮ
ጣዕሙ አይታወቅም የዚች አለም ኑሮ
ቀኙ ካላበረ ከግራ ወዳጁ
ማጨብጨብ አይችልም የሰዉ ልጅ በአንድ እጁ
የተደላደለ ህይወት እንድንመራ
እንዲህ እንዳማረብን እንሁን በጋራ
ትዉልድ እንድንቀጥል ፍሬ እንድናፈራ
ነገን እያሰብ ዘሩን ዛሬ እንዝራ
በአንድ ጎጆ ጣሪያ ደምቀን አብረን ስንገባ አብረን ስንገባ
እልል እልል ይባልልን ጉሮ ወሸባ ጉሮ ወሸባ
በአንድ ጎጆ ጣሪያ ደምቀን አብረን ስንገባ አብረን ስንገባ
እልል እልል ይባልልን ጉሮ ወሸባ ጉሮ ወሸባ
አሁን አሁን አሁን አሁን
አሁን አሁን አብረን እንሁን
አሁን አሁን አሁን አሁን
አሁን አሁን አብረን እንሁን
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri