ልሂድ እኔስ ናፈቀኝ የደጋጎቹ የቆንጆዎቹ ሀገር
ፍቅርን ሰቶ መቀበል ልማዳቸው ነው ከጥንትም ያውቃል ሀገር
ልሂድ እኔስ ናፈቀኝ የደጋጎቹ የቆንጆዎቹ ሀገር
ፍቅርን ሰቶ መቀበል ልማዳችን ነው ከጥንትም ያውቃል ሀገር
♪
መገን የድሬ ልጅ መገን የሀረሩ
እንደ ሀገሩ ብና ነብስ ያረካል ፍቅሩ
ገና ሲሻገሩ አዋሽ ድልድዩን
አንዳች ነገር አለው የሚያስተዛዝን
ናዝሬት መተሀራ ቆላቆላውን
አገኝው ይዎን ወይ የአፋር ዳይሎይን
ጆሌ ከረዩን
ወረ አርጎባን
የትም ቤት ይውሰደኝ
የትም ቤት ያድርሰኝ
የትምቤት ይውሰደኝ
የትምቤት ያድርሰኝ
ያያያው መንገደኛው እግሬ
የማታ የማታ ድሬ ነው አዳሬ
ሀረር ነው ሀገሬ
ጭሮ ነው ምንደሬ
የአገር ልጅ አድባሬ
ገበና ሚስጥሬ
ካንተው ነው አዳሬ
እንደምን ነው ጀጎል (የገራገር)
አጥሩ በራበሩ (የገርአገር)
ዘወርዋራው መንገድ (የገርገር)
የታሪክ ማህደሩ (የገርገር)
ልጠይቅህ እንጂ እንዳው ለነገሩ
አማን በአማን ነው ሸር የለምበሀገሩ
አማን ኢማን አማን ነው ሸር የለምበአገሩ
አማን ሰላም ፍቅር ነው ሸር የለም በሀገሩ
♪
ልሂድ እኔስ ናፈቀኝ የደጋጎቹ የቆንጆዎቹ ሀገር
ፍቅርን ሰቶ መቀበል ልማዳችን ነው ከጥንትማ ያውቃል ሀገር
♪
እስቲ ልሳለመው ቅዱስ ገብርሄልን
አገኝው እንደሆን ቁሉቢ ልጁን
ደደር ሀረዋጫ ተወልዶ ጀርጀርቱ
እጣው መወደድ ነው መፈቀር እርስቱ
ከከሬል ሰሙሌ ጂጂጋ ሽላቦ
ኧረ ስንቱን ልጥራው
አቦ ተውኝ አቦ
አቦ ተውኝ አቦ
አቦ ተውኝ አቦ
የትም ቤት ይውሰደኝ
የትም ቤት ያደርሰኝ
የትም ቤት ይውሰደኝ
የትም ቤት ያድርሰኝ
ያያያው መንገደኛው እግሬ
የማታ የማታ ድሬ ነው አዳሬ
ሀረር ነው አገሬ
ጭሮ ነው ምንደሬ
የአገር ልጅ አድባሬ
ገበና ሚስጥሬ
ካንተው ነው አዳሬ
እንደምን ነው ጀጎል (የገራገር)
አጥሩ በራበሩ (የገር አገር)
ዘወርዋራው መንገድ(የገራገር)
የታሪክ መሀደሩ(የገራገር)
ልጠይቅህ እንጂ እንዳው ለነገሩ
አማን በአማን ነው ሸር የለም በሀገሩ
አማን ኢማን አማን ነው ሸር የለም በአገሩ
አማን ሰላም ፍቅር ነው ሸር የለም በሀገሩ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri