ታድያ እንደምን ልመን አያዳላም ብዬ አምላክ ለፈቀደው መንፈሱ
እያሳየኝ በዓይኔ እያፈዘዘኝ በውበት በግርማ ሞገሱ
ታድያ እንደምን ልመን አያዳላም ብዬ አምላክ ለፈቀደው መንፈሱ
እያሳየኝ በዓይኔ እያፈዘዘኝ በውበት በግርማ ሞገሱ
ያደላል እንጂ ጌታ አሃ
አምላክ በጣም ያደላል (ያደላል ጌታ)
ለሁሉም እኩል ፀጋ (አሃ)
እስኪ መች ሰቶ ያውቃል (ያደላል ጌታ)
ያደላል እንጂ ጌታ አሃ
አምላክ በጣም ያደላል (ያደላል ጌታ)
ለሁሉም እኩል ፀጋ (ኦሆ)
እስኪ መች ሰቶ ያውቃል (ያደላል ጌታ)
ዞሬ እንዳየሁት የዓለምን ጓዳ በእጣፈንታ መንገዴ
በክፉም በደጉም አጀብ የሚያሰኝ ትዝታ አለ በሆዴ
ባለማወቄ እንዳልኮነን አደራ እየገባቹ
የታሰረውን ጩኸቴን ስሙኝ ፍቱልኝ እባካቹ
ጥረህ ግረህ ብላ ብሎ መታወጁ
ለሁሉም አይደለ የክተት አዋጁ አህ
ለፍቶ ያገኘውን አንዱ በጉለበቱ
ሌላው ከታቀፈው ተቀምጦ ቤቱ
ቢሰጠው ነው እንጂ የማታ የማታ
እድሉን አሟልቶ ለወደደው ጌታ
መቼም ምክንያት የለው ከዚህ የተለየ
ለታዘዘው ሎሌ ንጉስ እየለየ
አህ! ያደላል እንጂ ያደላል ያደላል ጌታ
እህ! እንዲህም አርጎ ያደላል የማታ የማታ
አህ! ያደላል እንጂ ያደላል ያደላል ጌታ
እህ! እንዲህም አርጎ ያደላል የማታ የማታ
ሆይ ሆይ ያደላል እንጂ ያደላል ያደላል ጌታ
እህ እንዲህም አርጎ ያደላል የማታ የማታ
ሆይ ሆይ
ታድያ እንደምን ልመን አያዳላም ብዬ አምላክ ለፈቀደው መንፈስ
እያሳየኝ በዓይኔ እያፈዘዘኝ በውበት በግርማ ሞገስ
ታድያ እንደምን ልመን አያዳላም ብዬ አምላክ ለፈቀደው መንፈስ
እያሳየኝ በዓይኔ እያፈዘዘኝ በውበት በግርማ ሞገስ
ያደላል እንጂ ጌታ አሃ
አምላክ በጣም ያደላል (ያደላል ጌታ)
ለሁሉም እኩል ፀጋ (አሃ)
እስኪ መች ሰቶ ያውቃል (ያደላል ጌታ)
ያደላል እንጂ ጌታ አሃ
አምላክ በጣም ያደላል (ያደላል ጌታ)
ለሁሉም እኩል ፀጋ (ኦሆ)
እስኪ መች ሰቶ ያውቃል (ያደላል ጌታ)
ዞሬ እንዳየሁት የዓለምን ጓዳ በእጣፈንታ መንገዴ
በክፉም በደጉም አጀብ የሚያሰኝ ትዝታ አለ በሆዴ
ባለማወቄ እንዳልኮነን አደራ እየገባቹ
የታሰረውን ጩኸቴን ስሙኝ ፍቱልኝ እባካቹ
አንዳችም ሳይሰስት ጊዜና ሰአቱን
እየመነዘረ ሲገብር እውቀቱን ሀ!
በሚኖር ገበሬ በላም አለኝ ሰማይ
ካበሩ ምንድነው ዝናብና ፀሀይ
ከሺ ሰራዊቱ ከሚያራምዳችው
ተሰልፈው ካሉት እንደየግብራቸው ሀ!
ከሁሉም ከሁሉም በፀጋ ስጦታ
አላዳላም እንዴ ለሰዎቹ ጌታ
አህ! ያደላል እንጂ ያደላል ያደላል ጌታ
እህ! እንዲህም አርጎ ያደላል የማታ የማታ
አህ! ያደላል እንጂ ያደላል ያደላል ጌታ
እህ! እንዲህም አርጎ ያደላል የማታ የማታ
By game
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri